ንግድ ምክር ቤት በአስመጪዎች ቅሬታ ላይ ከሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ጋር ሊነጋገር ነው

ከጂቡቲ ወደብ ዕቃቸውን ማንሳት ያልቻሉ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት መላ እዲፈልግላቸው ጠየቁ፡፡ ንግድ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ጋር ለመነጋገር ለሰኔ 19 ቀን 2004 ዓ.ም. ቀጠሮ ይዟል፡፡