የ‹‹አራት ኪሎው›› እና ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› ወግ
ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
ሲሳይ አጌና በቅርቡ በመጀመሪያ በጀርመን፣ ቀጥሎ በአሜሪካን ሀገር ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› የሚል ርዕስ ያለው መፅሐፍ አሳትሟል። በእርግጥ መፅሐፉ እስከአሁን ሀገር ቤት መግባት አልቻለም (ምናልባት ወደፊትም ላይገባ ይችላል) ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በኢትዮጵያ የነፃ ፕሬስ ታሪክ የጎላ አሻራ ካላቸው ጥቂት ጉምቱ እና ትንታግ ጋዜጠኞች አንዱ ነው። ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ በድህረ ምርጫ 97 በተነሳው አለመግባባት ስራ እስካቆመበት ዕለት ድረስ ‹‹ኢትኦጵ›› እና ‹‹አባይ›› የተባሉ ጋዜጦችን በባለቤትነት ይመራ ነበር። በተለይ ኢትኦጵ ጋዜጣ በእጅጉ ተወዳጅ ከመሆኗም ባሻግር በስርጭትም ግንባር ቀደም እንደነበረች ይታወሳል።