የኮለኔል መንግስቱ መጽሀፍ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተቸበቸበ ነው

በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ታተመ!

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 7 ቀን 2004 ዓ.ም. june 14, 2012)በጸሐይ አሳታሚ ድርጅት የታተመው እና በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕ/ት በኮለኔል መንግስቱ ኀ/ማርያም የተጻፈው ‘ትግላችን’ የተሰኘው መጽሀፍ የመጀመሪያ ክፍል ኢትዮጵያ ውስጥ ታትሞ በስፋት እየተሰራጨ ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ መታተሙን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።