በቫንኩቨር ጸደንያ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ለዋልድባ ገዳም ምህላ ተያዘ
“ትእቢተኛ ነገስታት የነበሩት እነ ናቡከደነጾር በጸሎት ተሸንፈዋል” አባ መላከጸሐይ አፈወርቅ
Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 710 ቀን 2004 ዓ.ም. June 17, 2012)፦ በቫንኩቨር-ካናዳ የምትገኘው ጸደንያ ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት አባ መላከ ጸሐይ አፈወርቅ በዋልድባ ገዳም አካባቢ እየተፈጸመ ያለውን የእርሻ ቁፋሮ እና በመነኮሳት ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት ለማስቆም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታይ ምእመናን ምህላ እንዲገቡ ጥሪ አስተላለፉ።