ሙባረክና የግብፅ አብዮት

የሠማንያ አራት አመቱ የቀድሞ አምባገነን ገዢ ሆስኒ ማበረክ ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ እያጣጣሩ ነዉ።ሙባረክን አምና የካቲት ከሥልጣን ያስወገደዉ የግብፅ ሕዝባዊ አብዮትም ሙባረክን በተኩት የጦር መኮንኖች ሕልቅቱ ተይዞ በመኖር አለመኖር መሐል እያቃሰተ ነዉ