የፕሮጀክት ጥናት መጓተት የቴክኒክ ሙያ ኮሌጆች ግንባታን አስተጓጎለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሐዊ የትምህርት ሥርጭት እንዲኖር ለማድረግ በ2004 በጀት ዓመት በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ሊገነባቸው የነበሩ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጆች፣ በካፒታል ፕሮጀክት ጥናት መጓተት ምክንያት ሳይሳኩ ቀረ፡፡