ከስድስት ጊዜ በላይ የትራፊክ ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃዳቸውን ሊነጠቁ ነው

የትራንስፖርት ባለሥልጣን ከአሁን ወዲያ ባጠፉ ቁጥር ለአሽከርካሪዎች ደረሰኝ እየተሰጠ መቅጣት ብቻ አይበቃም በማለት፣ ከስድስት ጊዜ በላይ የትራፊክ ደንብና ሕግጋትን በመጣስ ሪከርድ በተያዘባቸው አሽከርካሪዎች ላይ፣ የመንጃ ፈቃዳቸውን እስከ መሰረዝ የሚደርስ ዕርምጃ የሚወስድብትን ደንብ እንዳወጣ አስታወቀ፡፡