ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሌሎች ባለሥልጣናት የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ለመወሰን ቀጠሮ ተሰጠ

የሕወሓት መሥራች የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የዓረና ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ አስገደ ገብረ ሥላሴ ‹‹ጋህዲ›› በተሰኘው የትግርኛ ተከታታይ ቁጥር ሦስት መጽሐፋቸው ምክንያት ዓቃቤ ሕግ ‹‹በስም ማጥፋት›› በመሠረተባቸው ክስ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ በርካታ የሕወሓት አመራር አባላትና ጄኔራሎች መከላከያ ምስክርነት በመጥራታቸው፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ‹‹የመከላከያ ምስክሮች ቃል የሚያመጣው ለውጥ የለም›› በሚል ያቀረበውን መከራከሪያ አይቶ ለመወሰን ፍርድ ቤት ለሰኔ 14 ቀን 2004 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጠ፡፡