ትዝታ – ዲስ አለማየሁ ቅኝት –
መስፍን ማሞ ተሰማ
“ሀዲስ አለማየሁ…የኢትዮጵያ መንግስት በፈረሰ ጊዜ ከራስ እምሩ ጋር ሆኖ ስለነፃነቱ በሚጋደልበት ጊዜ ቆሞም ተቀምጦም ተኝቶም የሚያቃጥለው ያገር ፍቅር ልቡን እየቀቀለው፤ እንፋሎቱ እየገነፈለ አይኑን እንባ እየሞላ ስላስቸገረው በናቱ ስም “የኢትዮጵያ ልቅሶ” ብሎ ሀዘኑን ለወንድሞቹ ለኢትዮጵያውያን ለማካፈል ሲል በንባው የፃፈልንን የሚከተሉትን ቃላት ለሃሳባችሁ መሰረትና መሪ ይሆኑዋችሁዋል ስንል ተካፋይነታችንን እያረጋገጥንላችሁ ሀዘኑን በጎደለ ሞልተን ፅፈንላችሁዋል”