የአበበና የመለስ የG-8 ፍጥጫ ከንድፈ ሓሳብ አኳያ ሲታይ!! አንተነህ ሽፈራው

በጦር ሜዳ ውስጥ ብዙ ዓይነት የጦር ጀብዶዎች እንዳሉ አውቃለሁ:: ሆኖም ግን ከሁሉም ዓይነት የጦር ጀብዶዎች እኔን ሁልግዜ የሚያስገርመኝ ግን ፊትን ሳያጥፉ ፊት ለፊት ጠላትን መፋለም ሲቻል በጠላት ጥይት ተመቶ የወደቀን የጦር መኮንን (አዛዥ) ተሽክሞ ወደ ወገን ቃጠና ማሸሽም ታላቅ ወታደራዊ ጀብዶ ሆኖ ለከፍተኛ የማዕረግ ዕድገት የሚያበቃ መሆኑ ነው:: በዚህ ሁኔታ ከምርኮ ዳነ የተባለን አንድ ከፍተኛ የጦር ጄኔራልና ጄኔራሉን ተሸክሞ ያሸሸ አንድ ሚሊሽያ በአንድ ግዜ የሻምበልነት ማዕረግ እንደተሰጠው (አንድ መኮንን ጓደኛዬ አሳይቶኝ – በደርግ ግዜ ማለቴ ነው) አውቅ ስለነበር አበበ በG-8 Camp David ስብሰባ ላይ ለሰራው ጀብዶ “የብርጌድርነት ሳይሆን የሙሉ ጄኔራል ማዕረግ ይገባዋል” ብለው ብፁህ አባታችን በኢሳት/ESAT መናገራቸውን ሰማሁና የ85ሚልዮን ሕዝብ ክብርን የገፈፈንና አገራችን ታይቶ በማይታወቅ ብርቱ አደጋ ላይ የጣለን መሰሪ ፍፁር በዚያ መሰል ቆራጥ ውሳኔ አንገት ማስደፋት በመቻሉ እንኳን ደስ ያለህ፤ አሁንም ሹመቱ ጠንቶ ለአገርህና ለምትወደው ሕዝብህ ክብርና ነፃነት ይሁንልህ ብያለሁ::

በአቦ አባባል “የተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው” እንደሚባለው ሳይሆን አበበ በዚያች 30 ሰኮንድ የቆየችን የሕዝብና የአገር ብሶትና ዋይታ ለማስተጋባት የተኮሳትን የእውነት ቃታ ለመሳብ ከራሱ ጋር ምን ያህል ሙግት እንደገጠመ ሁላችንም በዐይነ-ሕሊና በሚገባ የምንገነዘበው ይመስለኛል:: አበበ ከእሊናው ጋር ሙግት የገጠመ መለስ ዐይኑን በጨው አጥቦ በማምታት ላይ የተጠመደ ቡድን መሪን ማዋረድ ከብዶት/ጠፍቶት ሳይሆን ስጋቱ በታላቁ አዳራሽ የተሰባሰቡት ታላላቅ ሰዎች ክብርና በአዳራሹ ላይ የሰፈነው ታላቅ ድባብ እንደሆነ በሚገባ እገምታለሁ:: አበበ ግን ከአገሩና ከሕዝቡ የበለጠ ክብር የለውምና ያችን ታላቅ ዕድል ማሳለፍ አልፈለገምና የመጣው ይምጣ ብሎ በቀልጣፋ አንደበት እጅግ በጣም ድንቅ ሥራ ሰራ:: መለስ በድርጊቱ ተደናግጦ ዐይኑ አበበን ፍለጋ ከመቅጽበት ቢወረወርም ከጎኑ የነበሩት ሦስቱ የአፍሪካ መሪዎች ግን በሕዝብ ቀጥተኛ ምርጫ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ ናቸውና የመለስ እንደዚያ ባለው መድረክ ላይ ከመጀመሪያውም በኦባማ መጋበዝ መቻሉ እነሱንም ጭምር ሳያሳፍራቸውና ሳያሳስባቸው እንዳልቀረ ከመለስ ጎን ካሜራ ውስጥ የገባውን መሪ ሁኔታ መመልክቱ ዐብይ ምስክር ነው::

አበበ በወቅቱ የሰራውን ዝርዝር ሁኔት እኔ ልተርክ ብል ነገር ማበላሽ ነውና ጭራሽ አልሞክረውም:: ሆኖም ግን አበበ በዲያስፖራው ውስጥ የፈጠረው መልካም አጋጣሚ ሳይበርድና በመለስ ላይ የተጠቀመባቸው ምህፃረ-ቃሎች ከሕዝባችን አህምሮ ሳይረሱ ተሎ ብዬ እውን አበበ በዋናነት የተጠቀመበት ምህፃረ-ቃል (አምባገነን) the word Dictator, “Meles Zenawi is a Dictator” “You are a Dictator” የሚለው ለመለስ የሚመጥን ነበርን?- – – ሌሎች መፈክሮቹ ግን ጭራሽ እንከን አይወጣላቸውም::
ይህንን ፍሬና እጅግ በጣም ገላጭ ቃል Dictator የሚለው የመለስን ድርጊት በህወሓት ውስጥና ህወሓትና መለስ አንድ አካል አንድ አምሳል ሆነው በአገራችንና በሕዝባችን ላይ የሚከተሉትን የጋር አቋም ገባ ብሎ በንድፈ ሓሳብ ደረጃ ነጣጥሎ በማየት ልዩነቶችን በትክክል ማወቅ መሰረታዊውን የአገራችንን ችግር ለይቶ ለማወቅ ስለሚረዳ አጋጣሚውን በመጠቀም ከንድፈ ሓሳብ ትንታኔ አኳያ አንዳንድ መስተካከሎች እንዲጨመሩና ወደፊት መለስንም ይሁን ሌሎች የእሱ የጎሳ ፓለቲካ ሰለቦች በተገኘው መልካም አጋጣሚ ሁሉ እውነተኛ ማንነታቸውን በሚገባ እንደምናውቅ ማሳወቅ ይጠቅማል በሚል እምነት ነው የግል አስተያየቴን ለማቅረብ የወስንኩ:: በተለይ መለስ ዜናዊ ዲያስፖራው ዛሬም ድረስ እውነተኛ ማንነቴን አላወቀኝም ብሎ እንዳይመፃደቅና አምባገነን መባሉን በፀጋ እንዳይቀበለው ለማድረግ ጭምር ነው – – – ምንም እንኳን በወቅቱ እጅግ በጣም ያባነነው ድርጊት ቢሆንም ቅሉ:: ይህን በማድረጌ ግን እኔም ሆንኩ ሕዝቡ ለአበበ ያለንን ክብርና አድናቆት በዚህ የንድፈ ሓሳብ ትንታኔ ወይም በሌሎች አባባል ‘የቃላት ስንጠቃ’ ይቀንሳል የሚል እምነት ጭራሽ እንደማይኖር በመተማመን ነው:: እርግጥ ነው በዚህ ጹሑፍ ገባ ብዬ ወደ ዝርዝር የንድፈ ሓሳብ ትንታኔ ለማቅረብ ባልፈልግም ቀጥዬ የማነሳው ጽንሰ-ሓሳቡ ግን ለሰፊ ውይይት መነሻነትም ሊያገለግል ይችላል የሚል እምነት አለኝ::

ወደ ዕለቱ ጉዳይ ስንመጣ ምንም እንኳን አቶ መለስ በህወሓት ውስጥ የለየለት አምባገነን እየሆነ የመጣ መሆኑ ባይካድም የወይኔ (የህወሓት) አመሰራረትና መሰረታዊ ዓላማዎች ከአገራችና ከሕዝባችን አኳያ ሲገመገም ግን በባህሪም ይሁን በይዘት የአምባገነንነት ባህሪይ ሳይሆን ሊይዝ የሚችል ዘረኛነትን(ጎጠኝነትን)ና ፋሽሽታዊነትን ነው:: እኛ በኢትዮጵያ ሉዐላዊነትና በሕዝባችን ዴሞክራሲያዊ አንድነት የምናምን ኢትዮጵያውያን አቶ መለስ በህወሓት ውስት አምባገነን ሆነ አልሆነ ጭራሽ አይመለከተንም:: እንደዚህ ያለው የህወሓት የውስጥ አስራር ችግር የሚመለከታቸው ቢኖሩ ህወሓትዊ አቋማቸውን ይዘው አቶ መለስን ብቻ በመቃወም ከህወሓት ድርጅታችን በአቶ መለስ ጫና ወይም ተንኮል ወጣን ወይም ተባረርን የሚሉትን ብቻ ይሆናል – – – ይህ ግን አቶ ገ/መድህን አርያን አይመለከትም፤ አቋሙ መለስን መቋወም ብቻ ሳይሆን ወይኔ አፈጣጠሩ ፀረ-ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በሚገባ ለይቶ ያስቀመጠ የቁርጥ ግዜ ወንድማችን በመሆኑ:: እናም አቶ መለስ በህወሓት ውስጥ ያለው ባህሪ አምባገነን ሊሆን ቢችልም ህወሓትና አቶ መለስ በኢትዮጵያና በሕዝባችን ላይ የሚከተሉት ፖሊሲ ግን አምባገነንነታዊ ባህሪ ሳይሆን ከላይ ለማስቀመጥ እንደሞከርኩት ዘረኛነትን(ጎጠኝነትን)ና ፋሽሽታዊነትን እውን ማድረግ ነው:: ይህን የጋራ አቋማቸውን እውን ለማድረግ ደግሞ አቶ መለስም ሆነ የህወሓት አባላት ተቻችለውና እጅና ጓንት ሁነው ነው የሚሰሩ:: እንዲያውም እያንዳንዱ የህወሓት አባል ይህን የጋራ ዓቋማቸውን ለማስፈፀም በሚንቀሳቀሱበት ግዜ ከአቶ መለስ እንኳ እጅግ በጣም እርቀው ቢሄዱ (ኢትዮጵያውያንን ቢገሉ፣ ንብረታቸውን ቢቀሙ፣ ቢያስሩና ቢያንገላቱ) ምንም ዓይነት ጫና አይደረግባቸውን – – – አበጃጅሁ ይባላሉ እንጅ::

ይህን አባባሌን ለማስጨበጥ ስል በግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም ለአበበ ድፍረት “በጀሮህ አተኛ” በምትለዋ ግጥሜ ውስጥ አንድ ስንኝ እንደሚከተለው ብዬ ነበር:-
ጀማሪው (ቀያሹ) ኢጣሊያ – የናዚ ጓደኛ OR ጀማሪው ፋሽሽዝም – የናዚ ጋደኛ
ቀጣዩ ወያኔ ጥርቅም ምንደኛ – የነሱ ድቅያ:: ቀጣዩ ወያኔ የነሱ ድቅያ – ጥርቅም ምንደኛ::

ይህችን ስንኝ ገባ ብዬ ከማየቴ በፊት አምባገነን የሚለውን ማየትን ስለማስቀድም ቀጥሎ ያለውን ትንሽ ትንታኔ እንመልከት:-
ዓለማችን በተለያዩ አገሮች የተለያዩ አምባገነኖችን አስተናግዳለች:: ዛሬም ድረስ አምባገነኖች በብዛት አሉ:: የሁሉም አምባገነኖች ባህሪ ዜጎቻቸው ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በመጠየቅ ሥልጣኑን እንዳይጠይቋቸው የሚቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ – – – ይህም እስከ ተራና አስቃቂ ግድያ ድረስ የሚያደርስ ይሆናል:: ይህን የሚያደርጉት ግን ጎሣን መሰረት በማድረግ ሳይሆን የዴሞክራሲያው መብቱን በሚጠይቅ ማንኛውም ዜጋ ላይ ሁሉ የሚፈፀም ድርጊት ነው::

ዜጎች የዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ሳይጠይቁ ሰጥና ለምበጥ ብለው የሚገዙ ከሆነ ግን በየትኛውም የአገር ክፍል ቢቀመጡ፣ የሚፈልጉትን ሥራ ቢሰሩ፣ ቢነግዱና ሰፊ ሀብት ቢያፈሩ፣ ቢማሩና ቢመራመሩ ደስታውን አይችሉትም – – – በስልጣናቸው እስካልመጡባቸው ግዜ ድረስ:: ምክንያቱም ዜጎች ቢማሩ፣ ሀብት ቢያፈሩ እነሱም ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን በሚገባ ይገነዘባሉና ነው:: ከምንም በላይ ደግሞ የአገር ሉዐላዊነት ከተደፈረ በዜጎች ዘንድ ጭራሽ ተቀባይነት ስለማኖራቸው በአገር ሉዐላዊነት ላይ እጅግ በጣም ጠንካራ አቋም አላቸው:: የአገርን ሉዐአላዊንት ከማስከበርም ባሻገር ለዚህ ለያዝነው ዘመን አይሁን እንጅ ብዙ አምባገነን መንግሥታት የነበሩ የአገራቸውን የኢኮኖሚ አንፃራዊ በሆነ ደርጃ አሳድገው የሁሉንም ዜጎቻቸውን የኑሮ ደረጃ የተሻለ ድረጃ ያደረሱ እንደነበሩ ብዙ መጥቀስ ይቻላል:: የኤሽያ አገሮችን መጥቀስ እንኳ ትተን የፒኖሽ – ችሊን መጥቀስ ይበቃል – – – ዞሮ ዞሮ አበበ እንዳለው የኤኮኖሚው እድገት ያለ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት ተቀባይነት ስለሌለው እንጅ!! የኢትዮጵያውን እጅግ ከሁሉም የከፋ ያደረገው ግን ከወያኔ ዘራፊዎች በስተቀር ሌላው ዜጋ ይብስኑ ሀብቱ እየተመናመነና ከቀየውና ከንብረቱ/ከቤቱ እየተፈናቀለ ያለ መሆኑ ነው::

የደርግ መንግሥት ከአምባገነኑ ባሕሪው ላይ ሶሻሊዝም የሚባለውን መጤ እምነት ከመኢሶንና ከኢህአፓ ተውሶ ብዙ ዜጎችን የጨፈጨፈ ቢሆንም ቅሉ መላኩ ተፈራ ያለ ርእራኤ የዘመተው በራሱ ቀዬ ልጆች ላይ ነበር – – – በትግሬው ገብረሂወት እየታገዘ:: እነ መላኩ በሥልጣን የመጡባቸውን ከመግደልና ካሳ ቢራ ይዞ ከመጠታት ያለፈ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብቱን ዘረፉ፣ ሕዝቡን በጎሣው ለይተው ገደሉ ቢባል ከንቱ የማይሆን ነገር ነው:: የአምባገነኖችን ባሕሪያት እጅግ በጣም ገባ ብሎ ነጥብ በነጥ ማስቀመጥ በተቻለ ነበር:: ሆኖም ግን ይህን በዚህ ትተን የወያኔን አመሰራረት ብንመለክት ከላይ በትቂቱ ስለአምባገነኖች ከቀረበው ፍፁም ይለያል:: የሚለይባቸው ቁልፍ መሰረታዊ እምነቶችም አሉት እነሱም:-

የተወሰነ የሕብረተሰብ ክፍልን ለበላይነታችን አደገኛ ነው በሎ ለይቶ በመያዝ ቢቻል ዘሩን ለማጥፋት ያ ካልሆነ ግን ፍፁም ለማዳከም እንዲቻል ድርጅቱ በነዚህ (ዘር በማጥፋትና ያ ካልሆነ ግን በሁሉም መንገድ በማዳካም) መርሆዎች ላይ ይመሰረታል::
As history and most scholars speak, including Assefa Negash M.D, the Nazis claimed that Ethiopia is a threat against white supremacy, and white colonialism in Africa while Italy/Fascist claimed that Ethiopia is the Black Threat or Danger to its rule.
ናዚ ኢትዮጵያን ለነጭ ዘር የበላይነትና ለአፍሪካ በነጭ ዘር መገዛት ፍፁም ፀር ነች ብሎ በ1930 መጀመሪያ ጀምሮ ኢትዮጵያን ለማዳከም ከፍተኛ የስለላ መረብ በአገር ቤት ዘርግቶ (የማዳከሙን) ሥራ ይፈፅም እንድነበር ቢታወቅም ፋሽስት ኢጣሊያ ደግሞ ከበፊትም ጀምሮ ኢትዮጵያ ለአስተዳደሯ የማትመች አደገኛ አገር ብሎ ጥላሽት ይቀባታል:: Similarly, according to TPLF’s manifesto of 1968 EC and its founding racist platform Ethiopia is absolutely and deliberately reduced to Amara, and, pinpointed Amara as a very dangerous race to Tigray supremacy and its rule, and by any means and method no matter whether Tigray is part of Ethiopia or not, it has to be either exterminated as a race or weaken and marginalized from the Ethiopian political dynamics. Therefore, Meles ruling system has to be characterized based on these facts rather than his dictatorial behaviour within his racist TPLF organization as it is none of our business.

ምንም እንኳን መለስ በህወሓት (በወያኔ) የውስጥ ጉዳይ አምባገነን ነው ቢባልም ቅሉ ኢትዮጵያን ለማዳከምና አማራ የሚባልን ዘር ለማጥፋት፤ ይህ ጭራሽ የማይቻላቸው ከሆነ ደግሞ ለማዳከም ባላቸው የጋራ ድርጅታዊ አቋማቸው እጅግ በጣም ተቻችለውና የውስጥ ልዩነታቸውን አቻችለው (ወይም የመለስን በህወሓት የውስጥ ጉዳይ ያለውን አምባገነናዊ ባህሪውን ችለው) እየሰሩ ነው::
ለዚህም ወያኔ (ህወሓት) አማራ የሚለውን የሕብረተስብ ክፍልና ሌሎችም በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ ዜጎችን ለይቶ በመግደል ላይ ይገኛል፣ ከቤት ንብረታችው እንዲፈናቀሉ አድርጓል/አሁንም እያደረገ ነው፣ ልጆቻቸው በበሽታ እንዲሞቱ አድርጓል/አሁንም እያደረገ ነው፣ የትምህርት ዕድል እንዳያገኙ አድርጓል/አሁንም እያደረገ ነው፣ ከኤኮኖሚው ሙሉ በሙሉ እንዲገለሉ አድርጓል/አሁንም እያደረገ ነው፣ አንዳንድ የተማሩ ቢኖሩም ስራ እንዳያገኙ አድርጓል/አሁንም እያደረገ ነው፣ ስራ የተሰጣቸውም ቢሆን የራሳቸውን ጎሳ እንዲወጉለት አድርጓል/አሁንም እያደረገ ነው፣ አልያም እርስ በእርስ እንዲጋጩ ያደርጋል፣ አማርኛ ተናጋሪው ቁጥሩ ከዕለት ዕለት እንዲቀንስ (depilated) ከመደረጉ በላይ ተመደበ የሚባለው ዓመታዊ በጀት ትግራይ ውስጥ ለአራት ወራት በተደራቢነት ከሰራ በኋል አምጥተው ቢሰጡትም በተያዘው የዓመቱ የግዜ ገደብ ውስጥ መሰራት ያለበት ሥራ/ፕሮጀክት ስለማይሰራ የተመደበው በጀት እንደገና በፈሰስ ወደ በጀት መዳቢው ክፍል እንዲመለስ ተደርጎ ወደ ወያኔ የግል ካዝና ገቢ ተደርጓል/አሁንም እያደረገ ነው::

ወያኔ አማራ ብሎ አማርኛ ተናጋሪ የሆነውን የሕብረተስብ ክፍል ለማጥፋት ድርጅታዊ ዓላማው ያድርገው ይሁን እንጅ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ ኦሮምኛ ተናጋሪ የሆኑ በኦነግ አባልነት ሥም፣ በጋምቤላ፣ በአፋርና በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከአማራ ጋር እየተገደሉና ከቀያቸው እየተፈናቀሉ መሆኑ ጭራሽ መረሳት የለበትም – – – የጉራጌ ማኅበረስብ አባላትን እነ ተፈራ ዋልዋ ጭራሽ ሳያፍሩና ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በጎደለው ቋንቋ “ውሪንጫላ” የሚል ስያሜ እንደሰጧቸው በአደባባይ የተደመጠ የከሃዲነት ድርጊት ነበር:: ተፈራ ዋልዋ ወያኔዎች አማራኛ ተናጋሪ ለሆነው ማህበረሰብ “አህያ” ብለው የሚጠቀሙበትን ትንታኔ መጠቀሙ ነው ታላቁን የጉራጌ ማኅበረሰብ “ያህያ ልጅ/የአማራ ልጅ” እሰከማለት ድረስ እጅግ በጣም እርቆ የሄደ!! በትግራይ አጎራባች ክ/ሀገራት ያሉት (እነ ጎንደር፣ ወሎና አፋር) ግዛቶች ብቻ ሳይሆን ለትግራይ ተወላጅ የሚሰጡት በጋምቤላ ነዋሪውን ሕዝብ ከአያት ቅድመ አያቱ ባድማና ቀዬ እያፈናቀሉ ለሙን መሬታችውን ከወሰዱት ውስጥ 70% ኢንቭስተር የሚባሉት የትግራይ ተወላጆች ናቸው:: እንደዚህ ያለው አስተዳደርና አመራር በባህሪውም ይሁን በይዘቱ አምባገነናዊነት (dictatorial) ሳይሆን ጎሠኛነትና ፋሽስታዊነት እንደሆነ መለየት ይኖርብናል:: እናም መለስ (ከነ ሙሉ ህወሓት አባላቱ) ጎሠኛና ፋሽስታዊ (the hybrid of Racist and Fascistic) መንግሥት መሆኑን በሚገባ እንደምናውቅ እሱም ሆነ ወደፊት እሱ ባለበት የስብሰባ አዳራ ውስጥና አደባባይ የሚገኙ ታዳሚዎቹ በግልፅ ሊነገራቸውና ሊያውቁት ይገባል::

ምንም እንኳን ወያኔ ካለፉት ረጅም ዓመታት ጀምሮ በዋና መልኩ ፀረ-አማራ ሆኖ ቢንቀሳቀስምና ሌሎችንም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲወክሉ ባደራጃቸው ሰለቦቹ ለዚህ እኩይ ዓላማው በተለያየ ጥቅማ-ጥቅም እያታለለና እየደለለ ለግዜው ሊያሰልፍ ቢችልም ከአማራ ማኅበረሰብ መዳከም (ወይም መጥፋት) በኋላ ደግሞ ዐይኑን በጨው አጥቦ በኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖቻችና በሌሎች ላይ የሚፈጽመው መሆኑ መረሳት የለበትም – – – ምክንያቱም የአደረጃጀት ባህሪውና ፖሊሲው ነውና:: ከዚህም ግንዛቤ በመነሳት ነበር ምንም እንኳን አማርኛ ተናጋሪ በሚባለው ማኅበረሰብ ላይ በአራቱም አቅጣጫ ያ ሁሉ ግድያ በተጠናከረ መልኩ በሚከናውንበት እጅግ በጣም ዘግናኝ ወቅት ፕ/ር አሥራት ወ/የስ ኢትዮጵያን ከወያኔ የጥፋት አደጋ ለመታደግ መደራጀት የሚያስፈልገው በአማራነት ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ጽኑ እመንት መሆኑን በማመን ለመደራጀት ወያኔን ፈቃድ የጠየቁት:: ወያኔ ግን የሚዋጋው ኢትዮጵያዊነትን ነውና ፕ/ር አሥራት የኢትዮጵያ ድርጅት መሪ ሆነው እንዳያደራጁ ፈቃዱን በመከልከል በኢትዮጵያዊነት ድርጅት መመሥረት እንደማይቻልና ከፈለጉ ግን በአማራነታቸው እንዲደራጁ ፈቃድ ለመስጠጥ እንደሚያስብበት የነገራቸው:: ፕ/ር አሥራት የወያኔን ሰንካላ አካሄድ በሚገባ የተገነዘቡ ቢሆንም ሌላ አማራጭ አልነበራቸውና በመዐሕድ ድርጅታዊ ፕሮግራም ሽፋን ገጽ ላይ ብቻ መዐሕድ የሚል እንዲነበብበት አድርገው ውስጥ ድርጅታዊ ፕሮግራሙን ግን ያልተምታታ ኢትዮጵያዊ አቋም እንዲይዝ አደረጉ:: ይህን የተገነዘቡ የሌላ ማኅበረሰብ አባላትም መዐሕድ የሚለው ስያሜ ሳያግዳቸው በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ከፕ/ር አሥራት ጋር ለመቆም ቃል እንደገቡ በሚገባ አውቅ ነበር:: አንዳንድ ግለሰቦች ግን በአማራነት መደራጀትን ፕ/ር አሥራት እንደፈለጉት አድርገው ሲናገሩ ስሰማ እጅግ በጣም አዝናለሁ:: እውነቱ ግን እኒሁ ግለሰቦት የሚሉት አልነበረም::

እንዲያውም የፕ/ር አስራት ወ/የስ ኢትዮጵያዊነት አቋማቸው ፍፁም ግልጽ እየሆነ ሲሄድ በአገር ውስጥ አማራጭ ያጡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በመዐሕድ ዙሪያ ይበልጥ እየተደራጁና መዐሕድን ለማሳደግ ከፍተኛ ርብርብ በማድረጋቸው ምክንያት ወያኔ እጅግ በጣም ተደናግጦና የሚይዝ የሚጨብጠው ሁሉ አጦ ዐማራ ለሚባል ድርጅት ፈቃ መስጠቱ ዞሮ ዐማራ (ኢትዮጵያውያን) የሚባሉትን ይበልጥ ለመለየት ጽ/ቤቱን ተጠቀመበትና ጭራሽ የማይረሳ ማሳደድና ጭፍጨፋ አደረገ፤ ፕ/ር አሥራትንም በዚያ መልክ ለእልፈተ-ሕይወት ዳረጋቸው:: እናም እውነት ዛሬ በዚች አገር ዴሞክራሲያዊ እኩልነትና ሰላማዊ ሕይወት እንዲኖር ከፈለግን ሁላችንም ከጎሣ ፖለቲካ ሰለባነት ተላቀንና አቋማችን ተሎ አስተካክለን ፀረ-ወያኔውን ትግል ከሚዲያ ጦርነትና ግርግር ባሻገር በተጨባጭ መንገድ በጋራ ማፋፋም ሊታለፍ የማይገባ ነው::

በጎሣ ተደራጅተው በሕዝባችን መካከል ጥላቻ የዘሩና የሰላማዊ ዜጎቻችን ሕይወት በከንቱ እንዲጠፋና ኢንዲፈናቁል ያደረገ ሁሉ ያለምንም ማመንታት በሕግ ፊት ተጠያቂ እንደሚሆኑ በግፅ ማስቀመጥ አለብን:: ጎሠኝነት የትም አያደርሰንም:: ወያኔ በአማር ሕዝብ ላይ ከሚፈጽመው ግድያ ባሻገር በትግራይ ውስጥ ብቻ እንኳ እጅግ ብዛት ያላቸው ፋክተሪዎችና የንግድ ተቋማትን እያንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት አንድ እንኳን አማራ በሚለው ክልል እንዲኖር ካለመፈለግና በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በኦጋዴንና በመሳስሉት አካባቢ ወገኖቻችን ከሚፈፀመው ተመሳሳይ ግድያ የበለጠ ዘር የማጥፋት ወንጀል የለምና የወያኔ ጎሣ ፖለቲካ ሰለቦች (እንደ ኦነግ የመሰሉት) ራሳቸውን ቆም ብለው በማየት ከጎሠኝነት ማነቆና ድርጊታቸው ተላቀው/እንዲቆጠቡና ኢትዮጵያንና ሕዝቧን በመታደግ ሁላችንም በእኩልነትና በዴሞክራሲያዊ አንድነት በሰላም ለመኖር፣ የጋራ አገራችንን ባለን ችሎታና እውቀት በአስቸኳይ ለማሳደግ፣ ለመገንባትና እንዲሁም ወያኔን ትጥቁን አስፈትቶ ለፍርዳ ለማቅረብ በወሳኙ የጋራ ትግል ላይ መረባርብን ግዜው የግድ የለናል::

እዚህ ላይ አንድ መታወቅ ያለበት ጉዳይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ በጎሣ/በጎጥ/ መደራጅት በሕግ እንዲታገድ ካልተደረገ ሁሉም ዜጎች በዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ መንገድ ተቻችለው ለመኖርና የአገር ሉዐላዊነትን በጋራ ሆነ ለማስከበር ፍፁም የማይታሰብ ነው::
ቀጥላ ባለችው አጭር ግጥም ውስጥ አልፎ አልፎ በቅንፍ ውስጥ ያስቀመጥኋቸው በመስመሩ ላይ ያለውን ስም ወይም ዘመን ወይም ፍሬ ነገር የበለጥ ግልፅ ለማድረግ ብዬ ቢሆንም ቅሉ ባነባበቡ ላይ ችግር እንዳይፈጥርባችው በውስጠ ታዋቂነት ባዐይናችሁ ገረፍ አድርጋችሁ ብቻ እለፉት::

“. . . በጎጥ ሳይመተር . . .”
አገር የጋራ እንዳይሆን እየተጣጣሩ
እነዚ ጎጠኞች ስንት ጥላቻ ዘሩ – ስንት አረም አፈሩ
አማራን በኢትዮጵያ – ኢትዮጵያን በአማራ እያቀያየሩ
ስንት ዜጋ ገድለው – ስንቱን አባረሩ::
ወልቃይት ተናገር ሁመራ ተናገር
አሩሲ ተናገር – አርባ ጉጉ ተናገር – ደቡቡ ተናገር
ሐረርም ተናገር – ጎጃምም ተናገር – ጋምቤላ ተናገር
ጅረቱ ተናገር – ተራራው ተናገር
ተከዜ ተናገር – ቃሌማ ተናገር
ተናግሮ የለም ወይ – መስክሮ የለም በቱሲዎች አገር
በውኃ ላይ አንሳፎ ሰውን በሰው እልቂት እጅግ ዘግናኝ ነገር::
ፀጋዬ (ደብተራው) ተናገር – አንተንስ ጣሉህ የት
የጦሩ አዛዡና የግዛቱ ንጉሥ – የአሁን ገብሩ አሥራት
የባንቱስቶች አለቃ መሪ የህወሓት
ዘመን አመጣሹ ንጉሠ ነግሥትት
አንተ የምትለው የፋሽስት ሠራዊት::
ስለምትንቃቸው ባለህ ጽኑ እምነት
ስንቱን ፊትህ ገለው ስንቱን ሰው አሰሩት
ስንቱን አንገላቱት ስንቱን አባረሩት
ስንቱን አፈናቅለው ለጎጠኛ (ለታጣቂ) መሩት::
አክሱም አረጃጅቶ – ዛጉኤ ድል ቀንቶት
(ባአስራ-አስረኛው ዘመን) ስልጣኑ ሲዛወር ወሎና ወልቃይት
የታሪክ አዋቂ የታሪክ መዛግብት
ሁሌም እንደሚሉት እንደመስክሩት
ተለክፈው ቀሩ አሉ (እኒህ ወያኔዎች) በታችነት ስሜት::
ብዙ ነገር ሆኖ – አልፎ ብዙ ዓመታት
ኢትዮጵያ ቅርፅ ይዛ ባባህር በወንዙ በአራቱ ማዕዘናት
ይህ ያስቆጣቸው ያካባቢ አገራት
ባላጣ ዘሩብን ክፉ የውስጥ (ያገር) ጠላት::
መሓሉ ተጎድቶ በመላኩ ድርጊት – በዓሊ ሙሳ ድርጊት
በካድሬዎች ድርጊት- አገር አልወልድ ብላ የጀግና ምልክት
ግዜ ዘንበል ብላ – ኢትዮጵያ ተዳክማ በምድረ መናፍቅት
በዐረብ እርዳታ ወያኔ ድል ቀንቶት – ዱባን ቅሉ ሰብሮት
ሁሌም ተጋዳላይ – ሁልግዜ ግድያ ከቶ ምን ዓይነት ሽንት
እርካብም ጨብጠው ወይ አለመተለቅ – ወይ አለመጨመት
ሁልግዜ ስርቆት -ወንድ የማይገባውን ክብሩን የእናት ማጀት::
የእድገትህን ክዕደህ በሹካ ብትበላ – ለመሆን ሮማ
ላቲኑን ብትመርጥ ልዩነት ፍለጋ – ለመሆን አውሮፓ
ይብቃ ምፅድቁ አትሁኑ መሳለቂያ
በእኔ ይሁንብህ “ፍንፊኔ” ቅኔ ነው አይደለም ቁ . . ት
እናንተ የምትጠሉት የፀጋዬ (የሁለትም-ፀ) አንደበት
የነ ያሬድ ልሳን የሙሴ ሚስት (የኢትዮጵያ) አባት
የጥንት የጠዋቱ (ቋንቋ) የሊቀ ሊቃውንታት::
ትርጉሙ ፍል-ውኃ በአማርኛ ቋንቋ
በፊት የነበረ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ የዝሆን መፈንጫ – የአጋዝን ሚዳቋ::
ዕድሜ ለጣይቱ ጭራሽ አማረበት ሆነ አዲስ አበባ
የመስከረም እምቡጥ የፀደይ አበባ
(ጎጠኛ ያዘው እንጅ) ለመሆን የቻል የጦቢያ መዲና – የአፍሪካ መዲና::
እረ ተው ይብቃ እስኪ አደብ ግዙ – ክፋ አንነጋገር
አገሩ ጦቢያው (ሰፊ) ነው የነ ካሌብ አገር – የኢዛና አገር
የቴዎድሮስ አገር – የምኒልክ አገር – ያባ-ጅፋር አገር
ያዓሊ ሚራህ አገር -የነፍጠኞች (የነመክት/ባልቻ) አገር
ለሁሉ የሚበቃ ጭራሽ ሳይሰፈር – (እንደ ቅርጫ ስጋ) በጎጥ ሳይመተር – – – በጎጥ ሳይመተር – – – በጎጥ ሳይመተር::

አንተነህ ሽፈራው!!