በኃይሌ ገብረ ሥላሴ ላይ የተመሠረተው ክስ እንዲቋረጥ ተደረገ

“ክሱ የተመሠረተው ያላግባብ ስለሆነ መከሰስ አልነበረበትም” የየካ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በአትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ላይ መሥርቶት የነበረውን “በሕገወጥ መንገድ መብትን የማስከበር ወንጀል” ክስ፣ “የማጣራው ነገር ስላለኝ ክሴን አቋርጫለሁ” በማለት ግንቦት 29 ቀን 2004 ዓ.ም አቋረጠ፡፡