“አሸባሪ” ፊልምም ይታገድ ጀመር
ከዚህ ቀደም ‹የባሕር በር› በሚል ርዕስ በጥላሁን ጉግሳ የተሰራው የአማርኛ ፊልም በኢቴቪ ማስታወቂያው እንዳይታይ ታግዶ የአንድ ሰሞን አወዛጋቢ አጀንዳ ለመሆን በቅቶ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፊልሙ ዋና ገጸ ባሕሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ‹‹በእኔ እምነት፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ አንድ ቀን መልሰው አንድ ይሆናሉ፡፡›› ብለው መናገራቸው ነው፡፡ ያለምንም ማጋነን መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ አንድ ሆነው ከሚያዩ ከሚና ሕንጻ ላይ ዓይናቸው እያየ ቁልቁል ቢወረወሩ ይመርጣሉ፡፡ የሻዕቢያን የጫካ ውለታን ኤርትራን እንደተገነጠለች በማስቀረት ነው የሚያረጋግጡት፡፡ እንዴያውም አንዳንዴ ሳስበው መለስ ከስልጣን መውረድ የማይፈልጉት ለሻዕቢያ እንደርሳቸው ታማኝ የሚሆን ኢትዮጵያዊ መተካት ስለሚከብዳቸው ይመስለኛል፡፡
ወደቀደመው ነገራችን ስንመለስ ትላንት አርብ፣ በኤድናሞል ማቲ መልቲፕሌክስ ሲኒማ መታየት የጀመረው ‘The Dictator’ የተሰኘ ፊልም እንዳይታይ ታገደየሚል ዜና አነበብኩ፡፡ መውጣቱን ከሰማሁ ጀምሮ በጉጉት ስጠብቀው የነበረው ይህ እምባና ሳቅ ያዘለ (comedy satire) ፊልም ሦስት ቀን እንኳን እንዳይታይ በመደረጉ ለእሁዴ ሳይደርስልኝ ቀርቷል፡፡ ግን ለምን የሚለው ጥያቄ አጭር ግምቴን እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ፡፡
በባሮን ኮኸን በገዛ ፊልሙ መሪ ተዋናይ የሆነበት ይህ ስላቃዊ ፊልም የጋዳፊ እና የሳዳም ሁሴን ድቅያ የሆነ አምባገነነዋ ገዢ ሆኖ የሚጫወት ገጸ ባሕሪ ፈጥሯል፡፡ ከፊልሙ ቅኝቶች ላይ ለማንበብ እንደሞከርኩት በርካታ የአምባገነኖች ባሕርያት የተሰገሰጉበት ይህ ፊልም፣ ከአንድ ወዳጄ እንደሰማሁት ደግሞ የኛውን ‹መለስ› ዜናዊን ቁልጭ የሚመስሉ በርካታ ትዕይንቶች አሉት፡፡ እናም የፊልሙ መታገድ ዋነኛ ምክንያት ከዚህ ውጪ ምን ሊሆን ይችላል?
በርካታ ጋዜጦች ታገዱ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ታገደ፣ በመንግስት ያልተወደዱ ዘፈኖች በመንግስት ይዞታ ስር ባሉ ሬዲዮ ጣቢያዎች እንዳይተላለፉ ታገዱ፣ አንዳንድ መጽሃፍቶች ሜጋ መጽሃፍት ማከፋፈያ ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ፣ የተቃዋሚ ድረገጾችና ጦማሮች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይነበቡ ታገዱ፣ የጀርመንና የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮዎች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሰሙ ታገዱ፣ …. ታገዱ፣ ታገዱ፡፡

Well done! I don’t hate Melles but he is not mandela. He is more like Idiamin.
The film is baned,
the film is about dictators,
the film is baned bacause its about dictators,
Dictaotors ban such kind of films,
THEEFORE, Meles/TPLF admits its dictatorship!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
Elias keep up the good job we are with you all the way]
አረሜነው መለስ አና ግብራ አበሮቹ ምን የማያባንናችው ነገር አለ የሰሩት ግፍ አና በደል ነው መርዝ አንድበላች ውሻ የሚያክለፈልፋቸው, አኩይ ድርጊታቸው አንዳይጋለጥ የማይሮጡበት ዳገት የማይወርዱት ቁልቁልት የለም ግን ፍጽሞ ያልተረዱት ነገር ቢኖር ከኢትዮጵያ ሕዝብ የሚድበቅ አንዳች ነገር አለመኖሩ ነው, ብቻ በዚህ አሉት በዚያ የኢትዮጵያን ሕዝብ የአፈና መረባቸውን ቀልብሶ አያነቀ ለፍርድ አሚቀርቡበት ጊዘ ሩቅ አይሆንም
would have been surprised if the headline reads as “Meles allows the dictatorship film….’
so,are you surprise! i am not what do expect from dictators.
M for dectaters
Meles,
Mobutu
Mengestu
Mubarek
የመለስ ደደብነት:: ፊልሙን ማገድ ማለት ነጻ ማስታወቂያ ለፊልሙ መስራት ማለት ነው:: ስንት ሰው ነው ኤድና ሞል ገብቶ ይህንን ፊልም የሚያይ:: 2000? አሁን በቭኢዲዮ እየተቀባበለ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ያየዋል::
መች በፊሩት ነው ቀኑ ሲደርስ ሁሉም በየተራ ይወድቃል እግዚአብህር ዝም ሲል የሚይያይ አይመስልም አይደል?