በተሽከርካሪ አደጋ 14 ሰዎች አለቁ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 01/02 ጥቁር ዓባይ ጠጠር መፍጪያ አካባቢ ግንቦት 28 ቀን 2004 ዓ.ም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ፣ ሌሎች ስድስት ሰዎች ደግሞ ከባድና ቀላል የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ዋና ሳጅን አሰፋ መዝገቡ አስታወቁ፡፡