አሥራት አንለይ ትዝታዬና መጽሐፉ

አሥራት አንለይወለላዬ (ከስዊድን)

… እራሱን የሚገል እራሱን የሚያድን

እራሱን የሚያስጠላ፤ እራሱን የሚሆን።

እኮ በሉ ጎበዝ! ይኸን ሰው እወቁት፤

ሲፈልግ የሚኖር፤ ሲፈልግ የሚሞት፤ …

አሥራት ለአሥራት

ትምህርት ቤት ለሁለት ወራት ሲዘጋ ለደብተር መግዣ የሚሆነኝ ገንዘብ የማገኝበት ስራ የሚያስቀጥሩኝ ዘመዶች ነበሩኝ። ሁለት ወይም ሦስት ክረምቶች ሰርቻለሁ። በኋላ እንደተረዳሁት ስራው በክረምቱ ወራት እንዳልወሰልት መቆጣጠሪያ ጭምር እንደነበር ልረዳ ችያለሁ።