የጠ/ሚ መለስ ባለቤት መሬት አላግባብ መውሰዳቸውን ያጋለጠው ሠራተኛ ታሰረ

W/o Azeb Mesfin ወ/ሮ አዜብ መስፍን (ማክሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2004 ዓ.ም. May 29, 2012)፦ በቅርቡ በቡራዩ ከተማ በከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በተመራው ሙሰኞችን የማጋለጥ ስብሰባ ላይ “ወ/ሮ አዜብ መስፍን ያለ አግባብ በወንድማቸው ስም መሬት ወስደዋል” ብሎ ያጋለጠው የማዘጋጃ ቤቱ ሠራተኛ መታሰር በከተማው መነጋገሪያ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ሪፖርተር መግለጻቸውን ጋዜጣው ዘገበ።