አራት የፌዴራል ፖሊሶችን የገደሉ ታጣቂዎች የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው
– በሁለት ፖሊሶች ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ግንቦት 24 ቀን 2004 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ሸንሌ ዞን ሆራ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ልዩ ስሙ ሰንደዲን በማለት በሚጠራ አካባቢ፣ በሥራ ላይ የነበሩ አራት የፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦችን በጥይት ደብድበው የገደሉ ሁለት ታጣቂዎች በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡