በፈረሰው ሊዝ ቦርድ ውሳኔ ይዞታዬን አጣሁ ያሉ ኢንቨስተር አቤቱታ አቀረቡ

–    ‹‹መብታችን ተነካ የሚሉ በመመርያው መሠረት ሊስተናገዱ ይችላሉ›› የቦሌ ክፍለ ከተማ

ከስድስት ወራት በፊት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ የፀደቀው አዋጅ ከመውጣቱ በፊት፣ የፈረሰው ሊዝ ቦርድ ይዞታን በሚመለከት ያስተላለፋቸው የተለያዩ ውሳኔዎች፣ የባለይዞታዎችን የማልማትና የባለቤትነት መብት እንዳሳጣቸው አንድ የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡