ሳዑዲ ዓረቢያ ለመሄድ የጤና ምርመራ ያደረጉ ከ20 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ውጤታቸው ተቀባይነት አጣ
– ለምርመራው ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍለዋል
በቤት ሠራተኝነት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ለመሄድ በነፍስ ወከፍ 550 ብር እየከፈሉ የጤና ምርመራ ያደረጉ ከ20 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ ‹‹የመረመሯችሁ የጤና ተቋማት የላኩት የምርመራ ውጤት ተቀባይነት የሌለውና የታገዱ ናቸው›› በመባላቸው፣ ውጤታቸው ተቀባይነት ማጣቱንና በችግር ላይ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡