ፍርሃት አዶ ከበሬ (አስቻለው ከበደ)

አስቻለው ከበደ

ደርግ ወደ ስልጣን መውጫው ጊዜ ላይ ድሮ ልጅ ሳለሁ አንድ የማይረሳ ትዝታ አለኝ። የጥምቀት በዓል ለማክበር ሄጄ አንድ ነገር ተመለከትኩ። አንዲት እናት የትግሬ ሽሩባ የተቆነደሉ በእጃቸው ረዘም ያለ ዘንግ ይዘው ከታቦቱ ፊት ጥቂት ሰዎች አጅበዋቸው ይሄዳሉ።