ጨዋታ ወፖለቲካ፡- ‘አንተ’ታ እና ‘አንቱ’ታ!

ሰሎሞን ተሰማ ጂ. (ከአ.አ.)

ይሄንንስ መቼም እነግራችኋለሁ። “ወሰድ ያደርግሃል እንዴ?” አይለኝ መሰላችሁ። መድኃኔዓለም ይውሰደውና። … አርባ-አራቱ ታቦት ይውሰዱትና! ምናባቱንስና ደግሞ እሱ ብሎ ባለ ዲግሪ! … እኔማ ልክልኩን ነገርኩት። “አሁን አንተ የማስተማር ዲግሪ ምናምን አለኝ እንዴት ትላለህ?” አልኩት። ልብ-ልቡን አሳጣሁት። “እኔ በግሌ ዲግሪህን ነጥቄሃለሁ!” አልኩና ቁርጡን ነገርኩት። አሃሃሃሃ …!!! ጭራ ሲያበቅል አየሁት። “… ስማ መልስልኝ፣ ምናምን እንዳትለኝ። ስማ! እኔ በግሌ ነው – ነጠቅኩህ – ያልኩህ፤” አልኩት። ይሄንንም መቼውንም እነግራችኋለሁ። …