ተወዳጁ የኢሳት ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ አረፈ

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 17 ቀን 2004 ዓ.ም. May 26, 2012)፦ ተወዳጁ የኢሳት ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ በደረሰበት ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከትላንት በስቲያ ሀሙስ ግንቦት 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ንጉሴ ጋማ በነጻው ፕሬስ ቀዳማይ ዓመታት ውስጥ በተለይም “ጧፍ” ትባል የነበረችው ተወዳጅ ጋዜጣን በዋና አዘጋጅነት፣ በኋላም “አዋሽ” ጋዜጣን በማኔጂንግ ኢዲተርነት ይመራ የነበረ ዕውቅ ጋዜጠኛ ሲሆን በወቅቱ ከፕሬስ ስራው ጋር በተገናኘ እስርና እንግልት የደረሰበት አይታክቴ ጋዜጠኛ ነበር።