አስተዳደሩ ያወጣው የአከራይ ተከራይ መመርያ ነጋዴዎችንና ፖሊሶችን አደባደበ

–    ከፖሊስ ጋር የተጋጩ ነጋዴዎች አንድ ቀን ታስረው በዋስ ተፈቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጥቅምት 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ባወጣው የአከራይ ተከራይ መመርያ ምክንያት፣ በአትክልት ተራ ነጋዴዎችና በሕግ አስከባሪ ፖሊሶች መካከል አለመግባባት በመከሰቱ መደባደባቸውን የዓይን እማኞች ገለጹ፡፡