ታዋቂው ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ አረፈ – ኢሳት
ኢሳት ዜና:- ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በጋዜጠኝነት ያገለግሉ ነበሩ:: በደረሰባቸው ድንገተኛ ህመም ለጥቂት ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::
ጋዜጠኛ ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ ባለትዳርና የ4 ልጆ ች አባት እንዲሁም የሁለት ልጆች አያት ነበሩ::
በጋዜጠኛ ንጉሤ ጋማ የህይወት ታሪክ ዙሪያ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም በቅርቡ ይዘን እንቀርባለን።
በዚህ አጋጣሚ ለጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ ቤተሰቦች፣ዘመድ አዝማዶች ጓዸኞች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በአገራችን እንዲረጋገጥ ያለመታከት በጽናት ሢሰራ የቆየው የነፃነቱ ዘብ ንጉሴ ጋማ በማረፉ ሀዘን ለተሰማችሁ በሙሉ፤ የኢሳት ዝግጅት ክፍል መጽናናት እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።