በአሸባሪነት የተከሰሰው ኬንያዊ የተጠቀሰበትን ክስ በሙሉ አመነ

–    ባላመኑት ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች እየተሰሙ ነው

ከአልቃይዳና አልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ባለፈው ማክሰኞ ማረሚያ ቤት ሆነው ክስ ከተመሠረተባቸው አምስት ተከሳሾች መካከል፣ የኬንያ ዜግነት ያለውና ሶማሊያ ውስጥ ይኖር የነበረው ሐሰን ጃርሶ የተጠቀሰበትን ወንጀል ሙሉ በሙሉ መፈጸሙን በሰጠው የእምነት ቃል አረጋገጠ፡፡