የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ይዞታና የመድረክ ወቀሳ

መድረክ ባሠራጨዉ ፅሑፍ እንዳለዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚገደሉ፥ የሚታሰሩና እንዲሰደዱ የሚገደዱት ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።መድረክ እንደሚለዉ መንግሥት ባለሥልጣናቱ በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርሱትን ግፍና በደል እንኳን አላስቆመም።