መለስ ዜናዊ "የአፍሪካ መሪዎች ሙስና ውስጥ የምንገባው በስግብግብ ኩባንያዎች ጫና ነው" አሉ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 4 ቀን 2004 ዓ.ም. May 12, 2012)፦ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ የአፍሪካ መሪዎች ሙስና ውስጥ የሚዘፈቁት በወጉ የተደራጁ የውጪ ኩባንያዎች የሚያደርሱትን ጫና ለመቋቋም ስለሚያዳግታቸው መሆኑን አመላከቱ። አቶ መለስ ይህን እምነታቸውን የገለጹት በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ለመምከር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ላይ ትላንት (ሐሙስ ግንቦት 2 ቀን) ከአንዲት የፎረሙ ተካፋይ ከሆነች ደቡብ አፍሪካዊት ለቀረበ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ነው።