የዋልድባ ገዳም ይዞታና የመነኮሳቱ ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ተጠየቀ
ለአቶ መለስ ዜናዊ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር – አዲስ አበባ)
ጉዳዩ፦ ታሪካዊ የዋልድባ ገዳማችን ይዞታና የመነኮሳት ሰብዓዊ መብት እንዲከበርልን ስለመጠየቅ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ታሪክ ማኅበራዊና ሥነ- ጥበብ እድገት ያበረከተችው አስተዋጽዖ ከኢትዮጵያ አልፎ በመላው ዓለም የሚታወቅ እውነታ ነው።