ለዶ/ር መስፍን አረጋ (ቦጋለ ዳኜ)

ቦጋለ ዳኜ – ከካሊፎርንያ

ለዶ/ር መስፍን አረጋ ሠላምታዬ ይድረሳቸው!

ዶ/ር መስፍን አረጋ ራማ ሉል በሚል ርዕስ ሰሞኑን በኢትዮሚዲያ ያወጡትን ጦማር አንብቤአለሁ። አማርኛን ብቁ የሳይንስ ማሰተማርያ ለማድረግ እንግሊዝኛን የሚተኩ ቃላት በራስ ቋንቋ ለመሰየም የሚያደርጉትን ጥረት አድናቂ ነኝ።