ዝቋላ ገዳም በቃጠሎ ዋዜማ ላይ ነው
·
ቦቴ
መኪናዎች ቢኖሩ ለውጥ ያመጡ ነበር፤
ቦቴ
መኪናዎች ቢኖሩ ለውጥ ያመጡ ነበር፤
·
መከላከያው
በሄሌኮፕተር እንዲረዳ ሊጠየቅ ይገባው ነበር፤
መከላከያው
በሄሌኮፕተር እንዲረዳ ሊጠየቅ ይገባው ነበር፤
·
የአዲስ
አበባ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ተሰባስበው ወደ ገዳሙ ሄደዋል፤
የአዲስ
አበባ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ተሰባስበው ወደ ገዳሙ ሄደዋል፤
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 10/2004 ዓ.ም፤ ማርች 19/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በምሥራቅ
ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ቀበሌ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ በሚገኘውና
የመንግሥት ይዞታ በሆነው ደን ምሥራቃዊ ገጽ ቅዳሜ ቀትር ላይ የተነሣው እሣት በመስፋፋት ገዳሙ አፋፍ ላይ መድረሱን ምንጮች እየገለጹ
ነው። ምእመናን የአቅማቸው በማድረግ ለማጥፋት ቢረባረቡም ሊቋቋሙት አልቻሉም።

ስለ ጉዳዩ የጠየቅናቸው ወገኖች እንዳስረዱን
ከሆነ ውኃ የመያዝ አቅም ያለቸው ቦቴ መኪናዎች፣ የወታደር ጉልበታም መኪናዎች ቢኖሩ ውኋውን ለማመላለስ ይረዱ ነበር። ነገር ግን
በዚህ ረገድ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጥያቄ እስካልቀረበ ድረስ እነ አ ምላሹም በአፋጣኝ እስካልተጠየቀ ድረስ የዚህ ታሪካዊ ገዳም
ህልውና የሰዓታት ዕድሜ ብቻ ነው ያለው ሲሉ ነግረውናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እሳቱን አሳሳቢነት የተረዱ
የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ከአዲስ አበባ በሦስት መኪና ወደ ሥፍራው ማቅናታቸው ታውቋል። እጅ በእጅ በተገኘው ሁሉ እሳቱን ለመከላከል
እየተደረገ ላለው ጥረት ድጋፍ እንደሚአደርጉ እናምናለን። ከደብረ ዘይት እስከ ናዝሬት ባለው አካባቢ ያሉ ምእመናንም ይቀላቀሏቸዋል
ብለን እንጠብቃለን።

ይህ ታሪካዊ ገዳም ያለውን መልክአ ምድራዊ
ይዞታ በተመለከተ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ “የብስራት እይታ” የጡመራ
መድረክ ከዚህ በፊት ያወጣቸውን ፎቶዎች እንድትመለከቱ እንጋብዛለን።

ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን