ስለ ዝቋላ ገዳም አሁን የደረስንበት … የዝቋላ ገዳም ቃጠሎ ግራ አጋቢ (ተኣምራዊ?) ትዕይንት እየታየበት ነው
·
እሳቱ በአንድ አካባቢ ኀይሉ ሲቀንስ/ሲገታ በሌላ ሥፍራ ድንገት እየተቀሰቀሰ የመከላከሉን ጥረት
አድካሚና ግራ አጋቢ አድርጎታል፡፡

“በምዕራብ ስናጠፋው በምሥራቅ እየዞረ፣ በምሥራቅ ስናጠፋው በምዕራብ እየዞረ፣ በተለይም ዐርብ ረቡዕ በሚባለው የተራራው ገጽ በኩል፣ ጠበል ሜዳን (ጠበሉ የሚገኝበትን ጥቅጥቅ ያለ ጫካ) እየከበበ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከገዳሙ በማእከላዊ ግምት ከ300 – 400 ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡”

በእሳት አጥፊ አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር በሚረጭ ኬሚካል ካልሆነ በቀር ከሦስት ቀናት በፊት
ጀምሮ ባፈር በቅጠሉ በሚደረገው የነፍስ ወከፍ መከላከል ጥረት ጨርሶ ሊጠፋ ወይም መጥፋቱ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡

እሳቱ ጠበሉ ወደሚገኝበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ከገባ ገዳሙ የነበር ታሪክ ይሆናል፡፡

· የተወሰኑ የአየር ኀይል እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ምእመናኑና ገዳማውያኑ
ከሚያደርጉት ውጭ የተለየ መከላከል ሊያደርጉ አልቻሉም፡፡
ከሚያደርጉት ውጭ የተለየ መከላከል ሊያደርጉ አልቻሉም፡፡
·
የውኃ
እጥረት እና የተራራው አቀበትነት ትግሉን አስቸጋሪ አድርጎታል።
የውኃ
እጥረት እና የተራራው አቀበትነት ትግሉን አስቸጋሪ አድርጎታል።
·
ዛሬ ቀን ላይ በሦስት መኪኖች ከአዲስ አበባ ተጉዘው ከስፍራው በመድረስ በተለይም እሳቱ አስቀድሞ
በተነሣበት ምሥራቃዊ አቅጣጫ (አዱላላ) ጥረት ሲያደርጉ ያመሹት ቁጥራቸው እስከ 300 የሚገምቱ በበጎ ፈቃድ የተሰበሰቡ የሰንበት
ት/ቤት፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እና በተለይም የአውቶቡስ ተራ አካባቢ ወጣቶች ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ናቸው፡፡
ወጣቶቹ፣ “ቃጠሎው በአንድ ቦታ
ኀይሉ ሲቀንስ/ሲገታ ባልታሰበ ሌላ አቅጣጫ ድንገት የመቀስቀስ ግራ አጋቢ እና ተኣምራዊ ጠባይዕ ያለው ነው፤” ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ለመንግሥት ደብዳቤ መጻፉ ተሰምቷል፡፡ ደብዳቤው ቃጠሎውን ለመከላከል
መንግሥት እገዛ እንዲያደርግና መንሥኤው እንዲጠና የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥንታውያን ገዳሞቻችን ህልውና እና ክብር
ላይ እየተጋረጠ በሚገኘው አደጋ በቂ ወይም ምንም ጥረት እንዳላደረጉ እየተወቀሱ የሚገኙት ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ነገ፣ መጋቢት
11 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በይፋ እንደሚፈጸም በሚጠበቀው የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 117ኛ ፖፕ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሲኖዳ
የቀብር ሥነ ሥርዐት ላይ ለመገኘት ዛሬ ማምሻውን ወደ ግብጽ እንደሚጓዙ ተዘግቧል፡፡ ከፓትርያርኩ ጋራ አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሌሎች ሁለት የፓትርያርኩ ፕሮቶኮል ሰዎች አብረዋቸው ይጓዛሉ፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን