የቴዲ አፍሮን አልበም የገዛሁበት ከመቶ በላይ ምክንያቶች
ፍቅር ይበልጣል
ከአንድ ደደብ ለአንድ ደደብ የተጻፈ አጸፋ
የቴዲ አፍሮን ልበም ለመግዛት ያየሁትን አበሳ አውቃለሁ። አልበሙን ለመግዛት የቋመጥኩትም ቴዲን በኢትዮጵያዊነት አርአያነቱ ከልቤ ስለማፈቅረው እንጂ ዘፈኑን – ገና ያላዳመጥኩትንና ያላጣጣምኩትን – ዘፈን በገና ለገና ወድጄ ወይም አፍቅሬ አይደለም። ይሁን እንጂ የቴዲን ዘፈን – ዘፈን ብቻም አይደለም ሙሾም ቢያወጣ – ተሸቀዳድሜ ኦሪጂናሉን እንደምገዛ ለራሴ ቃል ከገባሁ ቆይቻለሁ – ከመታሰሩ በፊት።