ሊቀ ጳጳሱ

የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በገዳሙ ሆነው የአደጋ መከላከሉን ሥራ እያስተባበሩ ይገኛሉ፡፡ አሁን በስልክ እንደገለጡልኝ እሳቱን የመከላከሉ ተግባር በወጣቶቹ በሚገባ እየተሠራ ነው፡፡  በፈቃዳቸው እና በራሳቸው ቁሳቁስ በኢትዮጵያዊ እና ኦርቶዶክሳዊ ወኔ ወጣቱ ትውልድ ያደረገውን ሃይማኖታዊ ተግባር አድንቀዋል፡፡
የአካባቢው ፖሊሶች ተጨማሪ የሰው ኃይል አያስፈልግም፣ ያለው በቂ ነው በሚል ሌሎችን ተጓዦች ያገዱ ሲሆን፣ ተጓዦቹ እንደገለጡት የያዙት ምግብ ማለፍ ባለመቻሉ እየተበላሸ ነው፡፡ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመቅረፍ እየሞከሩ ነው፡፡ ቢያንስ ውኃው እና ምግቡ እንዲያልፍ ለማድረግ፡
ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በገዳሙ ተገኝተው ቅዳሴ በመቀደስ፣ በወጣቶቹ እና በፖሊስ መካከል ችግ በተፈጠረ ጊዜ በማረጋጋት፣ እንደ ወጣቱ እኩል እሳቱን ተጋፍጠው ያሳዩት አባትነት በቦታው በተገኙት ወጣቶች ዘንድ አድናቆት እና አክብሮት አትርፎላቸዋል፡፡