የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች
የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በገዳሙ ስም ተከፍተው በየመረጃ መረቡ የተለቀቁ የባንክ ሂሳቦችን እንደማያውቋቸው እና ምእመናኑ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
አሁን በገዳሙ የሚደረገው የእሳት መከላከል ሥራ በበሚፈለገው መጠን እየተሠራ ሲሆን የአካባቢው ፖሊሶችም ዐቅም ያላቸውን ወጣቶችን በማስገባት ሥራውን እንዲያግዙ እያደረጉ ነው፡፡ በተራራው ላይ ሆነው የመከላከሉን ሥራ የሚያከናውኑት ወጣቶች በቦታው ላይ በቂ የሰው ኃይል መኖሩን እና የባሰ ነገር ካልመጣ በቀር አሁን ያለው ችግር በቦታው ላይ ካለው የሰው ኃይል ዐቅም በላይ እንደማይሆን ገልጠዋል፡፡
ገዳሙ በቀጣይ ለሌላ የእሳት አደጋ እንዳይጋለጥ የዝግጅት ሥራዎች መሠራት አለባቸው፡፡ ከፍተኛውን ገንዘብ የሚጠይቀው ሥራ ይኼ ነው፡፡ የአደጋ መጠባበቂያ መሣርያዎች በገዳሙ መቀመጥ አለባቸው፣ የእሳት ማጥፊያ መሣርያዎች ያስፈልጋሉ፤ የእሳት አደጋ መከላከያ መኮኒች የሚገቡበት መንገድ ያስፈልጋል፡፡ በቂ ውኃ የማጠራቀሚያ ገንዳዎች ያስፈልጋሉ፡፡ በዚህ ረገድ ከገዳሙ ጋር ተነጋግረን ወደፊት ለመግለጥ እሞክራለሁ፡፡ ዋናው የርዳታ ሥራ በዚህ ላይ ቢያተኩር ውጤታማ ይሆናል፡፡
