ውኃ ነገር


በዝቋላ ተራራ ላይ የተነሣው እሳት አሁን ወደ መብረድ የሄደ ይመስላል፡፡ ከነጋ እሳት እንዳልተነሣ በአካባቢው የሚገኙ ተከላካዮች ገልጠዋል፡፡ አሁን የቅዱሳን ከተማ በሚባለው በኩል እና በዓርብ ረቡዕ በኩል ከገደሉ ሥር ጢስ እየታየ ነው፡፡

በመከላከሉ ሥራ ላይ የሚገኙት ወጣቶች እንደገለጡልኝ አሁን በአስቸኳይ የሚያስፈልገው ውኃ ነው፡፡ ወደ ቦታው የመጡት የፌዴራል ፖሊስ አባላትም በውኃ አለመኖር ምክንያት የሚፈልጉትን ያህል ማከናወን አልቻሉም፡
የውኃ መጫኛ መኪኖች ያላችሁ ውኃ ሞልታችሁ በመሄድ የገዳሙን የውኃ ማጠራቀሚያ እንድትሞሉ ትለመናላችሁ፡፡