በመድፈርና አግቶ በማቆየት ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉት ‹‹የ24 ቀበሌ ልጆች›› እስራት ተፈረደባቸው

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸውን የአስገድዶ መድፈርና ከሕግ ውጭ ይዞ ማቆየት ወንጀል መከላከል ባልቻሉት ‹‹የ24 ቀበሌ ልጆች››፣ በሳምሶን ግዛቸው (ሳሚ ፋዬር) እና በዋሲሁን መኮንን ላይ ትናንትና የእስራት ቅጣት ውሳኔ ተሰጠ፡፡