ከሑመራ ከ140 በላይ ነዋሪዎች ታፍነው ወደ ኤርትራ ተወሰዱ

በትግራይ ክልል በቃፍታ ሑመራ ወረዳ በኤርትራ አዋሳኝ በሆነው የተከዜ ወንዝ ልዩ ስሙ ፅርግያ ግርማይ በተባለው አካባቢ፣ በባህላዊ መንገድ ወርቅ በማውጣት ላይ ተሰማርተው ከነበሩት መካከል ቁጥራቸው ከ140 በላይ ነዋሪዎች ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ታፍነው ወደ ኤርትራ መወሰዳቸውን በአካባቢው የሚገኙ የሪፖርተር ምንጮች ጠቆሙ፡፡