ዎልማርት የሸማቾች መፍትሔ ወይስ የነጋዴዎች ስጋት?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የዓለማችን ግዙፍ ኩባንያ በኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ሥራ ሊጀምር እንደሆነ እየተሰማ ነው፡፡ ዓመታዊ የሽያጭ ገቢው 4.5 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ የሚነገርለት የአሜሪካው ኩባንያ ዎልማርት፣ በሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ የገዘፈ ስምና ዝና አለው፡፡