አጼ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ በደራሲ ተስፋዬ ገ/አብ ዓይን

ገላነው ክራር ([email protected])

ተስፋዬ በሰሞኑ ጽሁፎቹ መነጋገሪያ ሆኗል። ጽሁፎቹን አነበብኩ። የተስፋዬን ጽሁፍ ሳያነብ የሚያልፍ ያለ አይመስለኝም። አሁን አሁን፣ በተለይም ካገር ከወጣ በኋላ የሚጽፋቸው አብዛኛዎቹ እውነትነት ቢኖርባቸውም፣ በርካታ ጉዳዮች ላይ በግልጽ መናገር ሳይችል እስካሁን አለ። በተረፈ ጽሁፎቹ በቋንቋ እየሰሉ የሄደ ፀሐፊነቱን ይመሰክራሉ። ተስፋዬ የአጻጻፍ ስሌቱ ውብ ነው። የግሌ ሃብቱ ነው።