እስኪ እንጠያየቅ፤ አገራችን የት ነው? (መጠባበቂያ ካስፈለገ)


ከመቶ ዓመት በፊት፣ በሃገራችን ሸንጎዎች የሚካሔዱት በተጻፈ ሕግ ሳይሆን በዳኞቹ የብልሐት ፍርድ ነበር፡፡ በምኒልክ ዘመን በዳኝነት ጥበባቸው ስማቸው ደጋግሞ የሚነሱት ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ናቸው፡፡ ካልተሳሳትኩ - ከዳኝነት ባንዱ የሚከተለው የገጠማቸውም እርሳቸው ናቸው፤ አንድ ሕፃን ልጅ ‹የኔ ነው፣ የኔ ነው› በሚል የተካሰሱ ሁለት ሴቶች ፍርዳቸውን ሽተው ቀረቡ፡፡

ኃብተጊዮርጊስ በጣም ተጨንቀው፣ አውጥተው፣ አውርደው ውሳኔያቸውን አሳለፉ፡፡ “እንግዲህ ሁለታችሁም እናት ነኝ ብላችኋል፡፡ ሁለታችሁም እናት መሆናችሁን ምስክር አቅርባችሁ አረጋግጣችኋል፡፡ እኔም ሁለታችሁም እናት መሆናችሁን አምኛለሁ፡፡ ስለዚህ ልጁ ለሁለት ተሰንጥቆ እኩል፣ እኩል እንድትካፈሉት ፈርጃለሁ፤” ብለው ወሰኑ፡፡

ውሳኔው እንደተላለፈ፣ አንደኛዋ ሴት ብትስማማም ሌላኛዋ ግን “በቃ ይቅርብኝ፣ ልጄ አይደለም፤ ትውሰደው” አለች፡፡ ይሄን ጊዜ ኃብተጊዮርጊስ “ልጁን ለመካፈል የተስማማችውን ሴት እንድትቀጣ ፈርደው ሲያበቁ፣ በልጇ መጨከን አቅቷት ‹ልጄ አይደለም› ለማለት ለበቃችው ሴት የእናትነት መብቷን አጎናጽፈዋታል፡፡

ከመቶ ዓመት በኋላስ?
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የደቡብ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡ ስለእርሳቸው ሰሞኑን ብዙ ያነጋገረን ፍርደ-ገምድልነት ከማውራቴ በፊት ባለፈው ሰሞን ተወርቶ የከሰመውን ገመናቸውን ማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡ ኢሕአዴግ በታሪኩ ያስተማረን ነገር ቢኖር፣ ለፓርቲው ታማኝ እስከሆኑ ድረስ የማይስተሰረይ ሃጢያት ብሎ ነገር የለም፡፡ ራሱ ኢሕአዴግ በቅርቡ በመሃላ እንዳረጋገጠልን የመንግስት ሌቦች ከመብዛታቸው የተነሳ፣ የሃገሪቱ ዋነኛ ችግር ሙስና ሆኗል፡፡ (በርግጥ እንደዛም ሆኖ ድህነት ቀንሷል፤ እኔም ብሆን በዚህ እስማማለሁ - ሙስና እስካለ ድረስ ድሃ የነበሩ ባለስልጣናት ሃብታም መሆናቸው አይቀርም፡፡)

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የካቲት 2004 ላይ በተካሄደው የደኢሕዴን ዓመታዊ ስብሰባ ላይ የሲዳማ ቡና ላኪዎች ማሕበር ባለአክሲዮን ናቸው፣ ሚሊዮን ብሮች መዝብረዋል የሚል ትችት ቀርቦባቸው÷ ‹ከተከሰስኩ ብቻዬን አይደለም ወ/ሮ አዜብ መስፍንም መከሰስ አለባት› ብለው ግምገማውን ረግጠው ወጥተዋል በሚል የተሰማውን የውስጥ አዋቂዎች ወሬ በርካታ ድረዓምባዎች ‹ነገሩ እንዴት ነው?› ብለውበታል፡፡ (ያኔ ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ችግር ሙስና መሆኑን በይፋ ሊያውጅ አንድ ወር ይቀረው ነበር፡፡) ነገርዬው እላይ ቤት በማነካካቱ ነው መሰለኝ ፍርዱ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል፡፡

ተፈርዶባቸው የማያውቁት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በክልላቸው የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪ ሰዎች ላይ ለመፍረድ ግን እምብዛም የተቸገሩ አይመስልም፡፡

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ በአንድ ወቅት ለethiopiafirst ድረዓምባ ስለብሔር ፌዴራሊዝም ጠቃሚነት ሲያብራሩ እንዲህ ብለው ነበር፡-

“በዚህች አገር ላይ የነበርን ዜጎች ሁለት ዓይነት ዜጎች ነበርን፡፡ አንደኛ፡- እኛ ገዢ ነን ብለው የሚያምኑ፤ የገዢ መደቦች ያሉባት፤ ሁለተኛ፡- በሃገራቸው፣ በመሬታቸው፣ በምድራቸው የማይኮሩ፤ ሁለተኛ ዜጋ ሆነው ተቆጥረው የሚኖሩባት አገር ነች፡፡ ይሄ ሁኔታ ነው የተቀየረው አሁን፡፡…. ይህንን ይዘን ግን …በመከባበር፣ በመደጋገፍ፣ በእኩልነት መንፈስ አንዲት ታላቅ እና ጠንካራ ኢትዮጵያ መገንባት እንችላለን፡፡”

እርሳቸው ‹አንደኛ፤› ብለው የተናገሩትን ስሰማ ትዝ የሚለኝ ያለፈ ነገር አይደለም፡፡ የአሁኒቷ ኢትዮጵያ ናት፡፡ እንደዘረኝነት አትቁጠሩብኝና ‹አሁን፣ በኢትዮጵያ የገዢው ፓርቲ መደብ (ብሔር) ማነው?› ብዬ ብጠይቃችሁ በእያንዳንዳችሁ አእምሮ ውስጥ የሚውጠነጠነው የተለያየ መልስ ነው የሚል ስጋት የሚያድርብኝ ይመስላችኋል? በፍፁም እንዳይመስላችሁ፤ ሁላችንም የምንረዳው ሐቅ አንድ ነው፡፡

ለመሆኑ እርሳቸው ራሳቸው ‹በመከባበር፣ በመደጋፍ፣ በእኩልነት መንፈስ› ትገነባለች የሚሉን ኢትዮጵያ “አንተ የዚህ ቋንቋ ተናጋሪ ስለሆንክ በዚህ ክልል መኖር አትችልም፤” ብሎ ደብዳቤ በሚጽፍ ክልላዊ አስተዳደር እና የብሔር ፌዴራሊዝም ነው ብለው ያምናሉ? እርሳቸው ቢያምኑስ እኛ እንድናምናቸው ይፈልጋሉ?

ዛሬ የጉፉራ ፈርዳ ሰዎች ናቸው በአስተዳደራቸው ቀጭን ትዕዛዝ ከቀያቸው በቋንቋቸው ጦስ የተሰናበቱት፡፡ ነገስ፤ ማነሽ ባለተራ?

9 Comments on “እስኪ እንጠያየቅ፤ አገራችን የት ነው? (መጠባበቂያ ካስፈለገ)”

  1. እነዚህ ተፈናቃዮች ክየት ነው ወደ ደቡብ የተሰደዱት? ለምን? በተወለዱበት ቀየአችው ለምን መኖር አልቻሉም? እስክ መች ይህ የተደበቀ ሰራ በአገር ስም ይነገዳል? ቀደም ብለው በሰፈሩትም ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ቢወሰድ መልካም ነው. አማራ ወደ ደቡብ ዘምቶ መረት ካልነተክ ወይም ግዛት ካላስፋፋ ኢትዮፕያ የምትተፋ ከሆነ ትትፋ. ይህ ድሮ የተለመደ እና ለዛረው ችግር መሰረት የነበረው አደጋ ነው.

  2. That was King Solomon, not Habtegiorgis. I.E, the story about the two mothers and the baby. It is an old-old-old story recorded first in the Old Testament. (perhaps other older similar stories may exist, as most biblical stories had their older version in other cultures and languages)

    As to Shigute, I don’t think he is the person we should point our finger at. He is no morethan a pupet at the end of a string. The pupetmaster pulls the strings.

  3. ስላም እናንተ አማሮች 7 አመት ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሰፍራችሁ በ7 አመት ከሃገራችን ተፈናቀለን ሰትሉ አታፍሩም?

  4. ሺ ብትለፋ, ሽፈራው ሽጉጤ እንደሆነ የወያኔ አሽከር መሆኑ የተረጋገጠ ነው:: እውነተኛው ወንጀለኛ ስብሃት ነጋ እንጅ ምስኪኑ ሽፈራው ሽጉጤ አይደለም:: ማን ምን እንደሆናችሁ ለማወቅ 20 ዓመት ከበቂ በላይ ነው::

  5. yegermal!!!!!!!

    The wise judgement was not of Habtegiorgis!!! Funny stupid! Wushetam!!! That was of King Solomon!
    Be afetarik yebeletsege hizb!Your wisdoms are all afetarik! that’s wat dragging us behind!

  6. የዚህ ጹሁፍ አቅራቢ-የ ሃብተጊዮርጊስ ብልህ ፍርድ በለክ የ ጻፍከው ነገር-የ ንጉስ ሰለሞን ጥበባዊ ፍርድ እንጅ የ ሃብተጊዮርጊስ ብልሃት አይደለም-ምናልባት እሳቸው ከ መጸሃፍ ቅዱስ ተምረው ይሆናል:: እና አስተካክል::

  7. ማናችሁም ሃብተጊዮርጊስ ወይም ሰለሞን ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አትችሉም:: ስለዚህ ሰውየው የሰጠውን ስም ቸል ብላችሁ ሃሳቡን የማጋሩ ከሆነ ተናገሩ:: ምክንያቱም ግለሰቡ ሰውን ማወደስ ሳይሆን የፈለገው ሃሳቡን በምሳሌ ማስደገፍ ነው:: ትልቁ ነገር እያለ ይቺን ቅንጥብጣቢ ይዞ ለሙግት ወይ ለእርማት መነሳት ደካማነትና ችኩልነት ነው::

  8. ወያኔዎች ሕግ ክልል አማራው ያለቦታችው ሄደው ነው ያረስው አያላችው የምታናፍት እናንተስ ክጋቤላው ከኦሮሞው ከደቡቡ ክልል ምን ትስራላችው እዚያው ኮረት ወደሆንው ምድራችው ለምን አትመልሱም ማንም ኢትዮጵዊ ክልሌን ከሉልኝ አስምሩልኝ አላላችውም ደግሞስ እናንተ መጣችሁብት እንጂ አልመጣባችውም ተበድሎ እና ተሽከማችው ባኖራችው አላስቆም አላስቀምጥ አላችሁት ይሀ ተራው ምስኪን ህዝብ ምን ያድርጋችው ሕገ መንግስት የምትሉት ስለ የትኚው ሀግ ነው የምታወሩት ይሀንን ስውን የምትገሉብት የምታስሩበት የምትገርፉበት ከቄየው የምታፈናቅሉብት አኮ የቱ ነው በመጀምሪያ ደረጃ ለቀረጻችው ሀግ ተገዥ ሳትሆኑ አና አንደፈለጋችው ሰርዛችው የምትደልዙት ሀግ ሕዝቡ እንዲያክብር መጠብቅ የለባችሁም አናንተ ከወጣችሁት ከሞተው ሕጋችው በላይ የኢትጵያ ሕዝብ ተፈቃቅዶ አና ትከባብሮ የኖረ ነው ወድፈትም ይኖራል ስለዚሀ ሕዝቡን በአጋዚ ጦር ቀስፋችው የያዛቹት ልቀቁት የዚያን ጊዘ ትልቅነቱን አስተዋይነቱን ታዩታላችሁ ደደብ የዘረኛ ጥርቅም ሁላ

  9. እኔ በጣም ያዘንኩት ለባለ ሽጉጡ ሽፈራው ነው ከወያኔ ሴራ መማር የማይችል ደደብ ስለሆነ መለስ ስለ አዜብ በተናገረው ነገር ቂም ሰለያዘበት እንደዚ አይነት ህዝብን ከጫፍ እስከጫፍ የሚያስቆጣ ውሳኔ እንዲወስን አስደርጎታል አሁን ለብቻው ተገኝቷል የቀን ጅቡ መለስ ቅርጥፍ አድርጎ ቢበላው እሰይ እንጂ የሚያዝንለት የለም ወያኔ ላለፍት አመታት
    አንዴ አማራን አንዴ ኦሮሞን ሲረግጥ የነበረው እንደዚ ባለ ሴራ ለየብቻ እየከፋፈለ እንጂ በአንድ ላይ ጥቃት ሰንዝሮ አያውቅም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*