1 Comment on “ጀርመን ራዲዮ 2 April 2012”

  1. ይድረስ ለአሜሪካ ድምፅ(ቭኢኦኤ)
    የአማርኛው ክፍል አዘጋጆች
    በአድራሻቸሁ::

    እንደምታውቁት ባለባችሁ የጋዜጠኝነት የሙያ ስነ-ምግባር አንጻር የዋልድባን ገዳም የተንኮል እሳት ሰደድ ለማጣራት ሕዝቡ መሃል በወኪሎቻችሁ አማካኝነት ገብታችሁ መረጃዎችን በማጠናቀር ዕውነቱ እንዲታወቅ አድር ጋችኋል::ይህም የትግል ውጤት በኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ይመዘገባል::
    በአንጻሩ ግን የመረጃ ሰጪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ሙያዊ ሥልት የመጠቀም ግዴታ እያለባችሁ ይህንን ባለማድረጋችሁ ግለሰቦች በጉጂሌው ቡድን ለግድያ እና ለእንግልት አደጋ ተጋልጠዋል::ይህም በመሆኑ ተጠያቂነት እንዳለባችሁ በትክክል በፖሊሲዎችና በዝርዝር መመሪያዎች ውስጥ መገለጹን ታውቃላችሁ::
    ስለዚህ ከላይ በዝርዝር የተገለፀውን መረጃ በማጣራት አስቸኳይ የተግባር ዕርዳታ ምላሽ እንድትሰጡ እየጠየቅኩ ወደፊትም ከሙያዊ ግዴታ አንፃር እና ከጉጅሌው የጭካኔ ባሕርይ አንጻር ለግለሰቦች ጥንቃቄ በመውሰድ አስፈላጊውን ጥበቃ እንድታደርጉ እጠይቃለሁ::

    ከማክበር ሠላምታ ጋር::

    ግልባጭ:
    –>ለጀርመን የአማርኛው ክፍለ-ጊዜ አዘጋጆች
    ለኢሳት የቴሌቭዥን እና ራዲዮ ዝግጅት ክፍል
    ለሚመለከታቸው በሙሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*