የእነአንዱአለም አራጌ የፍርድ ቤት ውሎ – መጋቢት 18

ከተከሰሱት ሃያ አራት ተጠርጣሪዎች መካካል ጋዜጠኛ እስክድር ነጋ ይገኝበታል። ዛሬ አዲስ አበባ ላስቻለዉ ፍርድ ቤት ተቃዉሟቸዉን ካሰሙት ተከሳሾች አንዱ ደግሞ ከተጠለሉበት ከሱዳን ስደተኞች ሠፈር ታፍነዉ ወደ ኢትዮጵያ እስር ቤት መጋዛቸዉን አስታዉቀዋል። የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በአሸባሪነት የተከሰሱ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን የመከላከያ ምስክሮች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ሲያደምጥ ዉሏል። የተቃዋሚዉ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ከፍተኛ ባለሥልጣን በሆኑት በአቶ አንዱአለም አራጌ መዝገብ ከተከሰሱት ሃያ አራት ተጠርጣሪዎች መካካል ጋዜጠኛ እስክድር ነጋ ይገኝበታል። ዛሬ አዲስ አበባ ላስቻለዉ ፍርድ ቤት ተቃዉሟቸዉን ካሰሙት ተከሳሾች አንዱ ደግሞ ከተጠለሉበት ከሱዳን ስደተኞች ሠፈር ታፍነዉ ወደ ኢትዮጵያ እስር ቤት መጋዛቸዉን አስታዉቀዋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ። ያዳምጡ

[podcast]http://radio-download.dw.de/Events/dwelle/dira/mp3/amh/E4C8946A_2_dwdownload.mp3[/podcast]