“ነጻው ሚዲያ” ስለ ቤተ ክርስቲያን ባለው አመለካከት “ነጻ” መሆኑን ያሳይ
- ኦርቶዶክሳዊ ፀሐፊዎች እየመሰሉ፣ በመግቢያቸው “ወያኔ ይውደም” የሚል ማባበያ ቃል እየጨመሩ ነገር ግን “ቤተ ክርስቲያን ትውደም” የሚለውን ግብ ያነገቡ ጽሑፎች በየዕለቱ ማንበብ ይዘናል።
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 26/2011፤ ጥር 18/2003 ዓ.ም)፦በተለምዶ “ነጻ ሚዲያ” እየተባለ የሚጠራው ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ የሆነውና በተለያዩ ግለሰቦች እና ቡድኖች የሚንቀሳቀሰው ሚዲያ ነው። “ሚዲያ” ያልነውን ራሱን ከለተመለከትነው ደግሞ የሕትመት ውጤቶችን ማለትም ጋዜጣና መጽሔቶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያውን ማለትም ሬዲዮና ቴሌቪዥኑን፣ እንዲሁም ድረ ገጾችን ሁሉ ያጠቃልላል። እነዚህን ሁሉ ጠቅልሎ በማጥናት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የሚያስተላልፉትን ለመመልከት ብዙ ጊዜ እና የሰው ኃይል እንዲሁም ገንዘብ የሚጠይቅ ቢሆንም በመጠነኛ የወፍ በረር (Birds Eye-view) ቅኝት ያገኘነውን ሐሳብ መነሻ አድርገን ትዝብታችንን ለመጠቆም እንደማይከለክለን እንረዳለን።
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)