የታክሲ ውስጥ ፅሁፎች

ሥነ-ልቡናዊ፥ ማሕበራዊ፥ ፖለቲካዊ፥ ሐይማኖታዊ እና ሌላም።ፅሁፉ ታኪሲና ብጤዎቹን ሙጥኝ ማለቱ ግን፥ የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ-እግዚ አብሔር እንደሚያወጋን፥ የባሕል፥የእምነት፥የፖለቲካ ጫና በአደባባይ የመናገር መብትን ማገዳቸዉን ጠቋሚ ነዉ። ላጭር ጊዜ ወደ አንድ አግጣጫ ከመጓዝ ባለፍ-ምንም የማይታዋወቁ መንገደኞች ባንድ አሳፍሮ ፊት-ለፊት አስቀምጦ የግድ ያሕል ለንግግር፥ ለወሬ፥ ለለከፋ፥ አንዳዴም ለተረብ፥ ጠብ በመጋበዙ ከመጓጓዣ-ታክሲነቱ ይልቅ አነጋጋሪነቱ አመዝኖ ዉይይት መጠሪያዉ ሆኖ ቀርቷል። ድሮ ጋሪ ፈረስ ላይ የደረሰዉ በሱም ደርሶ ከትላልቅ ከተሞች እያረቀ፥ ከገበያም እየወጣ ዘመኑ ያለፈበት ዉይይትን የተኩት ዘመነኛ ታክሲዮች እንደ ዉይይቱ በቃል-አላወያይ ብለዉ ነዉ መሰል በፅሑፍ ይዥጎረጎሩ ይዘዋል።ፅሁፉ ባብዛኛዉ አጫጭር ግን ቅይጥ ነዉ፥መልዕክቱም ብዙ።ሥነ-ልቡናዊ፥ ማሕበራዊ፥ ፖለቲካዊ፥ ሐይማኖታዊ እና ሌላም።ፅሁፉ ታኪሲና ብጤዎቹን ሙጥኝ ማለቱ ግን፥ የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ-እግዚ አብሔር እንደሚያወጋን፥ የባሕል፥የእምነት፥የፖለቲካ ጫና በአደባባይ የመናገር መብት-ድፍረትን ማገዳቸዉን ጠቋሚ ነዉ። ያዳምጡ

1 Comment on “የታክሲ ውስጥ ፅሁፎች”

  1. የፈለጋችሁትን መናገር ትችላላችሁ ነገር ግን በቅዱሳን መላእክት ቀልድ መቀለድ መቅሰፍት ነውና እንዳትቀሰፉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*