ትችትና ትዝብት፣ ሳቅና ቁምነገር፤ ታሪክና ተረት፡-
ተማሪ ተክሌ (ኦታዋ – ካናዳ)
1- ይሄ ጽሁፍ የተጻፈው ለለስላሳ አስተያየት እንጂ ለመረረ ውይይት አይደለምና ጊዜው የመዝናናት አይደለም የምትሉ ይሄንን ጽሁፍ በማንበብ ግዜያችሁን አትግደሉ።
2- “ግለሰቡን መደብደብ ትተን ምናለ ሀሳቡን ብቻ ብንተች” ይላል አንዱ የሰለጠነ ተቺ። ሌላኛው የሰለጠነ ተሳዳቢ ደግሞ “ድስት አጣቢ” ሲል ይሳደባል። አንዱ “አሁን ምናለ ይሄንን ሁሉ አተታ ለማተት ግዜ ባታጠፋ” ብሎ ሲል፤ “ይሄ ወቅቱን የጠበቀና ለብርቱካን መነሳት ያለበት ጥያቄ ነው?” ይላል ሌላኛው። የሚያስጨበጭቡም የሚያስደበድቡም ጽሁፎች መጻፍ ችሎታ ይጠይቃል ባልልም አንዳንዴ ትችትን ተቋቁሞ መጻፍ ድፍረትንና መቻልን ይጠይቃል።