የፖለቲካ እስረኞች የይቅርታ ጥያቄ

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዉ የታሠሩትና ጥፋተኛ ተብለዉም የተፈረደባቸዉ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ይቅርታ ለመጠየቅ መዘጋጀታቸዉ ሲነገር ቆይቷል። ስለጉዳዩ ከኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴር የይቅርታ ቦርድ እና የሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዛሬ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት ደግሞ የእስራት ብይን ከተሰጠባቸዉ ተከሳሾች መካከል የተባለዉን የይቅርታ ማመልከቻ ያቀረቡት አንዷ ብቻ ናቸዉ። ያዳምጡ