በጋምቤላ ክልል ከ4000 ሄክታር በላይ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን ተጨፈጨፈ
በጋምቤላ ክልል በአይነቱ ልዩ የነበረና ለዘመናት ተከብሮና ተጠብቆ የኖረ በመዠንገር ዞን ጎደሬ ወረዳ ጉማሬ ቀበሌ የሚገኝ ከ4000 ሄክታር በላይ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን እየተመነጠረ መሆኑን ዘጋቢያችን በቦታው የነበሩ አይን እማኞችን በመጥቀስ ከላከልን ዘገባ ለማወቅ ተችሎአል።
እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት ይህን ያህል ስፋት ያለውንና ለዘመናት ተጠብቆ የኖረ ደን እየጨፈጨፈ የሚገኘው ለእርሻ ልማት በሚል ሽፋን ዘረኛው አምባገነን አገዛዝ በሽያጭ ያስረከበው Vendata Harvests PLC. የተባለ የህንድ ኩባንያ እንደሆነ ታውቁአል ለቬንዳታ ኩባንያ የተሰጠዉ በተፈጥሮ ደን የተሸፈነዉ 4000 ሄክታር የሚሆን ለም መሬት የአካባቢዉን ኗሪዎችና እጂግ ማስቆጣቱንና አንዳንድ የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎችን እያነጋገረ መሆኑም ተያይዞ የደረሰን ዝገባ አሳይቱአል::
በተጠቀሰዉ ስፍራ የደን ጭፍጨፋውን እያካሄደ የሚገኘው የህንድ ኩባንያ የተፈጥሮ ደኑን መንጥሮ የሻይ ተክል ለመትከል መዘጋጀቱ የተገለጸ ሲሆን አንዳንድ ባለሙያዎች በተፈጥሮ ደኑ ላይ ሊከተል የሚችለውን ጭፍጨፋ በመገመት ቢያንስ ባለሃብት ተብየው ከሻይ ተክል የልቅ የቡና ተክል ቢተክል ቢያንስ ለጥላ ሲባል ከፊሉ የደን አካል ሊተርፍ ይችል እንደነበር ቢናገሩም ሰሚ አጥተው እንደቀሩ ታውቁአል ዘጋቢያችን ያናገራቸው አንድ የጎደሬ ወረዳ የግብርና ልማት ሰራተኛ የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ከሶስት በመቶ እንደሆነ እየታውቀ እንዲህ አይነት ውድመት መፈጸሙ ዘረኛው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ ሃገር የማጥፋት ተልእኮዉን በተግባር እያሳየ ለመሆኑ መረጃ ነው ብለዋል።
በቅርቡ በፈረንሳዊያን ተዘጋጂቶ ለእይታ የቀረበ ጥናታዊ ፊልም ኢትዮጵያ ውስጥ በልማት ሽፋን ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እያደረሰ ያለውን የሃገር ውድመት ያጋለጠ ሲሆን ይህ ፊልም በፈረንሳይና በስዊድን ሃገር የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች መተላለፉና በየሃገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን እጂግ ማሳዘኑ አይዘነጋም::
ወያኔ በሃይል ሥልጣን ከተቆጣጠረ ከ1983 ጀምሮ በትግራይ ክልል በየአመቱ ከፍተኛ የሆነ የዛፍ ተከላ ዘመቻ እያካሄደ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን ባለቤትነት በማይሰማው የአገሪቱ ደቡብ፤ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ክልሎች የሚገኘውን ጠቅጠቅ ያለ የተፈጥሮ ደን ያለምንም ርህራሄ እያስጨፈጨፈ እንደሆነ ግልጽ ሆኖአል።፡ ድህረ ምርጫ 97 በባሌ ክልል የሚገኘውን በደን የተሸፈነ ብሄራዊ ፓርክ ሆን ብሎ በ ዕሳት እንዲጋይ እንዳደረገና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እሳቱን ለማጥፋት በዘመቻ እንዲሄዱ ጠይቀው እንደተከለከሉ ይታወሳል።