ዘረኛው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ የሃይማኖት ተቁአማትን የማዋርደ ስራውን ቀጥሉአል
ከሁለት ቀናት በፊት በአዋሳ ገብሬል ቤተክርስቲያን በተነሳ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምእመናን መቁሰላቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ዘገበ እንደ ኢሳት ዘገባ ከሁለት ቀናት በፊት በምእመናን መካከል በተነሳ አለመግባባት በተፈጠረ ግጭት የቆሰሉ ሰዎች ወደሆስፒታል መወሰዳቸውን የተገለጸ ሲሆን ፣ የቅዱስ ገብሬል ቤተክርስትያንም ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉንና ምእመናኑም ወደ ቤተክርስቲያኑ እንዳይገቡ ተከልክለዋል፣ ውጥረቱ አሁን ድረስ እንዳለ ነው ብሉአል።
ኢሳት ከዚሁ ጋር አያይዞ እንደዘገበው የዘረኛው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ ባለስልጣናትና ለፍርፋሪ ጥቅም ሲሉ ለወያኔ በማደር እራሳቸውንና ወገናቸውን በማዋረድ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሆድ አደሮች በሃይማኖት ሽፋን የፖለቲካ ቅስቀሳ እያካሄዱ እንደሆነ አጋልጦአል። ወያኔ ሃይማኖታዊ ስብከት የሚሰብኩ ሰዎች ከመንግስት ፈቃድ እንዲወስዱ የሚያደርግ መመሪያ እየወጣ እንደሆነም አያይዞ ዘግቦአል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ግጭቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጎሎ መጥተዋል፣ ያለው ኢ ሳት ቀደም ብሎ የዘረኛው አምባገነን አገዛዝ ባለስልጣን ተፈራ ዋልዋ በምርጫ 97 ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የነፍጠኛው መሸሸጊያ ዋሻ ናት ማለቱን ፣ ኢህአዴግ የሙስሊሙ ህብረተሰብ አጋዥ ነው በማለትም ይቀሰቅስ እንደነበር አስታውሱአል።
የሃይማኖት ግጭቶች የድህነቱ የርሃቡና የመብት አፈናው መገለጫዎች መሆናቸውን ምሁራን ይናገራሉ ያለው ኢሳት ፣ አገዛዙ በሃይማኖት ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገቡ የይስሙላው ህገ መንግስት ቢደነገግም በስልጣን ላይ ያሉት የአምባገነኑ አገዛዝ ቁንጮዎች የሃይማኖት አባት ተብየዎችን እንደፈለጉት እንደሚያሽከረክሩአቸው ምእመናን ይናገራሉ ብሎአል።
የመለስ አምባገነን አገዛዝ በተለያዩ ጊዚያቶች ከኢትዮጵያ ህዝብ እየገጠመው ያለውን ፈተና ለመቋቋም የተለያዩ ስልቶች ሲጠቀም እንደቆየና ህዝብ እርስ በርሱ እንዳይተማመን ለማድረግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃይማኖት ዙሪያ መከፋፈልና ግጭት እንዲፈጠርም ሌት ከቀን እየሰራ እንደሆነ በተደጋጋሚ ስንዘግብ መቆየታችን አይዘነጋም።