ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የአዲስ አበባ ቤት አከራዮች 40 በመቶ ታክስ ክፈሉ አለ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩና የቤታቸውን ክፍል በማከራየት ኑሮአቸውን በመደጎም የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ከሚያገኙት ገቢ አርባ በመቶ ለአገዛዙ ገቢ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ ባስተላለፈው ዘገባ ገለጸ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም አዲስ አበባን ጨምሮ የሚገኙ ታላላቅ ከተማ ነዋሪዎች ሊቁዋቁዋሙት እያስቸገራቸው ያለውን የኑሮ ውድነት ለመጋፈጥ ከሚጠቀሙት ዘዴ አንደኛው ያለቻቸውን አነስተኛም ቤት ቢሆን እየከፈሉ፣ በማከራየት መጠነኛ ገቢ ማግኘት መሆኑ ይታውቃል።
ዘጋቢያችን ያነጋገራቸውና ቀደም ብሎ ከነበረቻቸው ሁለት ክፍል ቤት በአንደኛው እየኖሩ ሌላኛውን ክፍል በወር አራት መቶ ብር እያስከፈሉ የሚኖሩ ወይዘሮ እንደተናገሩት፣ ኑሮአቸውን እየገፉ ያሉት ከአነስተኛ ሸቀጣ ሸቀጥ ሽያጭ ገቢ በሚያገኙት ገንዘብ እንደሆነና ይህም ለኑሮአቸው ፈጽሞ ሊበቃቸው ባለመቻሉ ከሁለቱ ክፍል ቤት ሶስት ልጆቻቸውን ይዘው ወደ አንደኛው ክፍል ብቻ ለመኖር መገደዳቸውን ገልጸው በዚህ መንገድ ኑሮን ለመግፋት እያደረጉ ያለው ጥረት በደም መጣጩ ወያኔ አሁንም እየተደናቀፈ ነው በማለት በለቅሶ ተናግረዋል ቀጥለውም ቤታችንን ስንሰራም ሆነ ከዚያ በሁአላ ለኑሮአችን የሚበጅ አንዲትም ነገር ያላደረገ አገዛዝ ራሳችን ደም ተፍተን በሰራነው ቤት እንዴት ብሎ 40 በመቶ ታክሽ እንድንከፍለው እንደፈለገ አይገባኘም የያዝነው አመት ግፍ ሁሉ ሞልቶ የተረፈበት፣ ዘረኛው አገዛዝ ለህዝብ ያለውን ንቀት ከመቼውም በላይ አጉልቶ ያወጣበት ነው ብለዋል በመጨረሻም ወይዘሮዋ፣ ወያኔ በህዝብ ላይ እንዲህ ቀልዶና ግፍ ሰርቶ ረጂም ጊዜ እቆያለሁ ብሎ ማሰቡ ግን ከሞኝነት ያለፈ መጃጃል ነው ፣ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ዋጋውን ማግኘቱ አይቀሬ ነው ብለዋል።
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በተለይም በ1997 ዓም በተካሄደው ምርጫ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ አንድም መቀመጫ ወምበር እንዳያገኝ አድርጎ ጥላቻውን ከገለጸለት በሁአላ ተከታታይ የሆኑ የብቀላ ርምጃዎችን በህብረተሰቡ ላይ እየወሰደ እንደሆነ ይታወቃል።