የግብፁ ፓትርያርክ ቀብር
የሰማንያ ሥምንት አመቱ ሼኑዳ ሳልሳዊ ከግብፅ ሕዝብ አስር-በመቶ የሚሆነዉን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን በጥንቃቄ የመሩ ብልሕ መንፈሳዊ አባት እንደነበሩ ብዙዎች ይናገራሉ።በፓትሪያርኩ ሞት ፦ዛሬ በመላዉ ግብፅ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ ዉሏል
ባለፈዉ ቅዳሜ ያረፉት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስያን ፓትሪያርክ ሼኑዳ ሳልሳዊ ዛሬ በአንድ ጥንታዊ ገዳም ዉስጥ ተቀበሩ።በካይሮዉ የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል በተደረገዉ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት የሐገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፥ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች፥ የዉጪ ሐገራት ባለሥልጣናትና የሐይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል።የሽኝት ፀሎቱን የመሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ጳዉሎስ ናቸዉ።የሰማንያ ሥምንት አመቱ አዛዉንት ሼኑዳ ሳልሳዊ ከግብፅ ሕዝብ አስር-በመቶ የሚሆነዉን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን በጥንቃቄ የመሩ ብልሕ መንፈሳዊ አባት እንደነበሩ ብዙዎች ይናገራሉ።በፓትሪያርኩ ሞት ምክንያት ዛሬ በመላዉ ግብፅ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ ዉሏል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ-ሚካኤል ዘገባ አለዉ። ያዳምጡ
ለመላው ክርስቲያን ህዝብ በጣም አሳዛኝ መርዶ ነው:: በዚህ አጋጣሚም ለመላው የኦርቶዶክስ ሃይምኖት ተከታዮች ፅናቱን ይስጣችሁ አላለሁ
በጣም አሳዛኝ መርዶ ነው:
Rest in peace. You were great.
አቡነ ሽኖዳ አልሞቱም ወደ አገለገሉተ አምላካቸው ነው የሄዱት እኛን ያስቸገሩን በቁማቸው ሞተው ሰው የሚገድሉት አባት ሳይሆኑ አበት ናቸው አባ ጳውሎስ ሕያውን ለመቅበር ግብጽ ድረስ ወረዱ አሳቸው የገደሉትን ማን ያቃብራቸው ይሆን?