ዝቋላ እየነደደ ነው

ይህንን ጽሑፍ ስጽፍ እሳቱ ከተከላካዮች ዐቅም በላይ ሆኖ ወደ ገዳሙ በመዝለቅ ላይ ይገኛል፡፡ እሳቱ ገዳሙን ከወደ ሐይቁ በኩል እያጠቃው ነው፡፡ ከአዲስ አበባ እና ከደብረ ዘይት ተጉዘው በመከላከል ላይ የተሠማሩት ወገኖች ከዐቅማቸው በላይ እየሆነ ነው፡፡ እግዚአብሔር ካልረዳን ከሰዓታት በኋላ ታላቁን ገዳም እናጣዋለን፡፡

ውኃውን ከወንበር ማርያም ወደ ተራራው ለማውጣት መንግሥት የኡራል መኪኖችን እንዲተባበር የገዳሙ አበ ምኔት እየጠየቁ ነው፡፡ በስልክ ያገኘሁት እና በመከላከል ተግባሩ ላይ የተሠማራው ወንድም «አሁን ልንሸነፍ ነው፤ ታላቁንም ገዳም ልናጣው ነው፣ እሳቱ ፊት ለፊቴ እየመጣ ነው፡፡ እኛ መሸሽ እንችላለን፣ ገዳሙን ግን ምን እናደርገዋለን» ብሎኛል፡፡

(ኢሜይል [email protected])